ዋና ስራ አስኪያጁ ይህንን ያሉት ዛሬ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የገዳዲ ማሰልጠኛ ተቋም ስልጠና የወሰዱ ሰልጣኞች ባስመረቁበት ወቅት ነው፡፡የሰዎች አስተሳሰብ ላይ ካልተሰራ የህንጻም ሆነ የቴክኖሎጂ ጋጋታ ትርጉም የለውም ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ እንደ ከተማ አስተዳደር ተቋማት በሰው ሃይል መገንባት አለባቸው ተብሎ እየተሰራ ያለውን ስራ የሚያግዝ እና ተስፋ የሚሰጥ ስራ በባለስልጣኑ እየተሰራ መሆኑን ከሰልጣኞች ንግግር ተረድቻለሁ ብለዋል፡፡አቶ ጥራቱ የውሃና ፍሳሽ ስራ ከባድ ፣ መሰጠትን እና በፍቅር መስራትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው፤በከተማው ያለው የውሃ ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም በመልካም አገልግሎት ካልታጀበ ችግሩን የጎላ ስለሚያደርገው ሰልጣኞች በቆይታቸው ያገኙትን በጎ ነገር ወደ ስራ በመቀየር በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ዋና ስራ አስኪያጁ የባለስልጣኑ አመራሮችም ሆኑ ስልጠናውን በገንዘብ የሚደግፉ ተቋማት የሰራተኛው አስተሳሰብ ላይ እየሰሩ ላሉት ስራ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ለአምስት ቀናት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የባለስልጣኑ ሰራተኞችም ስልጠናው በአይነቱ የተለየ እንደሆነ ገልጸው፤ ባገኙት ትምህርት ከራሳቸው ጀምሮ በተቋማቸው ለውጥ ለማምጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ባለስልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ለውጥ የሚያመጣ Field Level Leadership (FLL) የተባለ ስልጠና በቪቴንስ ኢቪደስ ኢንተርናሽናል፣ በአለም ባንክ እና በባለስልጣኑ ትብብር እየሰጠ ይገኛል፡፡እስካሁንም ከ2000 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች ያሰለጠነ ሲሆን ከራሱ ሰራተኞቹ ባሻገር ከአፍሪካ ሀገራት ለሞዛምቢክ፣ ለኬኒያ እና ለጋና ከሀገር ውስጥ ደግሞ ለኦሮሚያ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ እንዲሁም ለባህርዳር የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሰራተኞች እና አመራሮች ስልጠናውን ሰጥቷል፡፡