የኘሮጀክቱ ሥም፡ በሶፍት ሎን የጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ልማት ፕሮጀክት
አስፈፃሚው አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት
ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በአዲስ አበባ የገጠር ከተማዎችና በአጐራባች የኦሮሚያ ገጠር ቀበሌዎች
ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣
የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- የጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ የመስመር ዝርጋታ ሥራ በማጠናቀቅ ወደ ሥርጭት ሲስተም በማስገባት የከተማዋ የንፁ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ቁጥር እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- የ26 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ፓምፕ ቴስት ሥራ ማከናወን፣
- የውኃ ማስተላለፊያ መስመር ኔትወርክ፣ ማጠራቀሚያ ጋንና የግፊት መስጫ ጣቢያ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ጥናት ማካሄድ
- የስርጭት (Transmission Line) መስመር እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ጥናት ማካሄድ፣
- ለተቆፈሩ ጉድጓዶች ወደ ማጠራቀሚያ ጋኖች መሰብሰቢያ (Collector pipes) የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
- የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች የዕቃ ግዥና ግንባታ፣
- የቧንቧና መገጣጠሚያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ውኃ ማጠራቀሚያ ጋን ግዥ፣
- የማጠራቀሚያ ጋን እና ሌሎች አስፈላጊ የህንጻ ግንባታ ሥራዎች፣
- የዋና መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
- የፓምፕና ጥበቃ ቤት ግንባታ እንዲሁም የትራንስፎርመር ተከላ ሥራ
- ከጉድጓድ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ የካሳ ክፍያ
- የግንባታ ሱፐርቪዥን ሥራ
ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-
- በ2004 ዓ.ም.
ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-
- በ2007 ዓ.ም.
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 1,685,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡
መግቢያ
የአዲስ አበባ ከተማን የውሃ ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት እቅድ ጐን ለጐን ከቻይና መንግስት በተገኘ የረዥም ጊዜ ብድር የሚሰራ ተጨማሪ ሥራዎችም በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ኘሮጀክቶቹ በአዲስ አበባ ገጠራማና በአነስተኛ መተዳደሪያ አቅም ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ያቀፈ ሲሆን በተለይ በመገንባት ላይ ለሚገኘው የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ተጠቃሚዎችም የተሻለ የውሃ አቅርቦት ማድረግን አላማ ያደረገ ኘሮጀክት ነው፡፡
ኘሮጀክቱ በ2005 በጀት ዓመት 26 ጥልቅ ጉድጓዶችን ለማስቆፈር ያለመ ሲሆን አጠቃላይ እንቅስቃሴው የጉድጓድ ቁፋሮና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች አቅርቦት፣ የሲቪል ሥራዎች፣ የመዳረሻ መንገድ ግንባታ እንዲሁም የማጠራቀሚያ ጋን ግንባታ ሥራን ያቀፈ ነው፡፡
የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት
ለብዙ ጊዜ የከተማው ሕዝብ መሠረታዊ ችግር ሆኖ የኖረውን የውሃ አቅርቦትና ስርጭት ችግር ለመቅረፍ ከመንግሥት በጀት በተጨማሪ የሚሰራው ይህ ኘሮጀክት በተለይ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈ ሲሆን በከተማው ውስጥ በሁሉም የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙትን የሕብረተሰብ ፍላጐት የሚያቅፍ ኘሮጀክት መቀረጹ ለመልካም አስተዳደር ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደረውን ሕብረተሰብ በቀላሉ የንፁሕ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ስለማያደርገው ለሕብረተሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
የኘሮጀክቱ ዓላማ
የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣
የኘሮጀክቱ ግብ
በበጀት ዓመቱ በቀን እስከ 70 ሺህ ሜ.ኪዮብ ውኃ ለማምረት የሚያስችሉ የ26 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ ሥራዎች ይጠናቀቃል፡፡
የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች
ኘሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን በአካባቢው በአነስተኛ ገቢ የሚኖረው የሕብረተሰብ ክፍል ቅድሚያ ተጠቃሚ ሲሆን የንፁሕ ውሃ ለማግኘት ብዙ መንገድና ብዙ ወጪ የማያወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በቀላሉ ተጠቃሚ ይሆኛሉ፡፡ በዚህም የአካባቢው ሕብረተሰብ የኑሮ ደረጃው ይሻሻላል፣ በተበከለ ውሃና በውሃ ወለድ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች ይቀንሣሉ፡፡ በአጠቃላይ የሕብረተሰቡ ምርታማነትና የኑሮ በማሣደግ በኩል ከፍተኛ ውጤት ይኖረዋል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት
- በዲፌክት ሊያቢሊቲ ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶችን ማስተካከል
- የመያዥያ ክፍያ መፈጸም
የአፈጻጸም ስልቶች
- በአዲስ አበባ ገጠር አካባቢዎችና በአጐራባች የኦሮሚያ ቀበሌዎች ለውሃ መገኛ የሚሆኑ አካባቢዎችን መለየትና የውሃውን ጥራትና የአካባቢውን ምርታማነት የሚቀንሱ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች መቆጣጠር፣
- ለተቆፈሩት ጉድጓዶች የሚሆኑ ፓምፖችና ቧንቧዎችን ማጠራቀሚያ ጋኖችን መግዛት፣
- አዲስ የተገነቡትን ጉድጓደች ከነባር ሲስተም ጋር በማጣጣም የግፊትና የመመለሻ መስመር ጥናትና ዲዛይን ማሰራት ግንባታ ማከናወን እና ቁጥጥር ማካሄድ፣
ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች
- ኘሮጀክቱን የሚያጠናና በግንባታም ወቅት ሥራውን የሚከታተል አማካሪ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በባለቤቱ በኩልም እንዲሁ ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶች ይመደባሉ፣
የአካባቢና የማህበራዊ ትንታኔ
በአማካሪ ድርጅት ከቀረበው አንዱና ዋነኛው ኘሮጀክቱ ሊያስከትል የሚችለው አካባቢያዊ ተጽዕኖ ግምገማና ኘሮጀክቱን ተከትሎ የሚመጡ የኢኮኖሚና ሶሻል በጎና አሉታዊ ተጽእኖዎች ናቸው፡፡
የተጠናውን ጥናት መሠረት በማድረግ አሉታዊ ተጽኖዎችን ለማስቀረትና በጎ ጐኖችን ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ ያሰራል፡፡
አጠቃላይ እና ዝርዝር በጀት
ባጠቃላይ በበጀት ዓመቱ የተጠቀሱትን ሥራዎች ለማከናወን ብር 43,256,000 የሚያስፈለግ ይሆናል፡፡
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
42 | የሶፍትሎን ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ልማት ፕሮጀክት | 43,256,000 | 0 | 200,000 | 43,056,000 | 0 | ||
42.1 | የመያዥያ ክፍያ መፈጸም | 1,722,240,000 | 43,056,000 | 43,056,000 | አጠቃላይ ሥራው ያለቀ በመሆነ የሚያዥያ ክፍያ 2.5 በመቶ የሚሆነው ብቻ በ2008 ተይዟል፡፡ | |||
42.2 | የሱፐርቪዥን ክፍያ መፈጸም | 200,000 | 200,000 | 200,000 | በውሉ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ከግንባታ ቁጥጥር ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከፈል በጀት ነው፡፡ |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች