የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ለማዘመን በከተማው ባስገነባቸው ከ40 በላይ የተማከሉ እና ያልተማከሉ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ነዋሪውን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚሁ መሰረት በስድስት ወራት ውስጥ የፍሳሽ መሰረተ ልማት በተዘረጋባቸው አካባቢዎች ለ31,755 አባወራ የፍሳሽ መስመር ቅጥያ ለማከናወን ታቅዶ ለ38,114 አባወራዎች መስመር በማገናኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ቅጥያ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል በንፋስ ስልክ፣ ጎፋ፣ ለቡ፣ ጎተራ፣ ቄራ፣ ላፍቶ፣ ማሞ ኮንዶሚኒየም፣ አየር ጤና፣ ኪዳነምህረት፣ ሚካኤል፣ ቤቴል፣ ወይራ ሰፈር፣ ዓለም ባንክ፣ ቆሼ፣ ወተት ቤት፣ ሚካኤል፣ አንፎ፣ ኬ3 ማጠራቀሚያ፣ ቤቴል አካባቢዎች፣ ፒያሳ፣ ካዛንቺስ፣ ሜክሲኮና አካባቢው፣ ካዲስኮ፣ አድማስ፣ ቃሊቲ ማጣሪያ፣ ቦሌ እና የካ ክ/ከተማ በከፊል፣ እንቁላል ፋብሪካ እና ሰሜን ማዘጋጃ ይገኙበታል፡፡