ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ 2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ከደንበኞች ፎረም አባላት ውይይት አካሄድ ።
ቅርንጫፉ ውሃ በፈረቃ እያደረስ ቢሆንም ቀድሞ ፈረቃው ይዛባ እንደነበር ገልጸው በአሁኑ ጊዜ የተሻለ አግልግሎት መኖሩን የፎረም አባላት ገልፀዋል ።
በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ ተቋሙ ወዝፍ ገቢ አሰባሰብ ላይ ክፈተቶች መኖራቸውን ገልፀው በቀጣይ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከፎረም አባለት እና ከየወረዳ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት ወዝፍ የመሰብሰብ ስራ በትኩረት መሰራት እንደለበት አባላቱ ጠቁመዋል ።
ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የውሃ መስረተልማት በከተማዋ እስከ 8ሺህ ኪ.ሚ የሚገመት የውሃ መስመሮች የሚገኙ ሲሆን የፎረም አባላት በየአከባቢያቸው የውሃ መስመሮችን እና መሰረተ ልማቶችን እንዲጠብቁ የጠቆሙት የቅ/ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ አርጋው በአከባቢያቸው የሚመጡ ማንኛውም የባለስልጣኑ ሰራተኛ የባለስልጣኑ መታወቂያና ባጅ ሳይዙ ከተገኙ ለሚመለከተው አካል በመጥቆም እንዲተባበሩ ጠይቀዋል ።