ባለስልጣኑ ለ12ኛ ዙር የመሪነት ስልጠና የወሰዱ ሠራትኞችን ባስመረቀበት ወቅት የተገኙት አቶ ይስሀቅ ተቋሙ በራሱ አሠልጣኞች እና በራሱ የስልጠና ማዕከል የውስጥ አቅሙን ለመገንባት እያከናወነ ያለውን ተግባር አበረታተው ቋሚ ኮሚቴው ለባለስልጣኑ ዕቅድ መሳካት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

አቶ ይስሀቅ በንግግራቸው ተገልጋዩን ህብረተሰብ ለማርካት እና የባለስልጣኑ አጋር ለማድረግ ሠልጣኞች ያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት ወደ ተግባር መቀየር አለባቸው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ በበኩላቸው የመሪነት ስልጠናው ሠራተኞችን የሀላፊነት እና የአገልጋይነት መንፈስ እንዲላበሱ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀው ፤ ወደፊት ማሠልጠኛ ማዕከሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።