ጉድጓዶቹ ስራ ያቆሙት ባለፉት ተከታታይ አምስት ቀናት ባጋጠመው የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ምክንያት ሲሆን ፓምፖቹን ጠግና ወደስራ ለመመለስ እየተሰራ ይገኛል።
ሆኖም ጥገናው ከ10 ቀናት በላይ ሊወስድ ስለሚችል በተለይ በሳሪስ፣ አዲስ ሰፈር፣ ቄራ፣ ሳር ቤት፣ ደምበል ጀርባ፣ ስታዲየም፣ ኤርፖርት እና ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢዎች የውሃ አቅርቦት ችግር ይፈጠራል።
ጉድጓዶቹ በቀን 17,539 ሜ.ኩብ ውሃ የሚሰጡ ሲሆን በእነዚህ ጉድጓዶች ስራ ማቆም ሳቢያ 159 ሺህ በላይ አባዎራዎች ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ።
በመሆኑ ደንበኞቻችን የፓምፕ ጥገናው ተጠናቆ መደበኛ የውሃ ስርጭት እስኪጀምር ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ከዚህም በተጨማሪ በሌሎችም የለገዳዲ፣ የአቃቂ ጉድጓዶች እና የግፊት መስጫ ጣቢያዎች ላይ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሀይል መቆራረጥ በውሀ ምርት እና ስርጭት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ኤሌትሪክ አገልግሎት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡን ጥሪ እናቀርባለን ።
<img class="j1lvzwm4" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
Comment
Share