የጥበቃ አባላቱ GBS ከተባለ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲ ጋር ውል በመፈጸም ወደ ስራ ገብተው የነበሩ ሲሆን በቀን 27/02/2013ዓ.ም የተለያዩ ቁጥር ያላቸው የቧንቧ መፍቻዎችን፣ ሁለት GPS እና የብረት መጋዝ መያዣ/ሰጌቶ ከዕቃ ከግምጃ ቤት ነው የሰረቁት፡፡
ተጠርጣሪዎቹም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ ሁለት በተለምዶ ስብሰባ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕቃዉን እንደተሸከሙ በአካባቢው ማህበረሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡
ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሰረቁት ቁሳቁሶች ከ23 ሺህ ብር በላይ ይገመታል፡፡
በቅ/ጽ/ቤቱ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት የቋሚ ንብረቶች ባለሙያ አቶ መክብብ ሙሉጌታ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ ቁሳቁሶች ሲጠፉ እንደነበር አስታውሰው ሌሎች የባለሥልጣኑ ቅ/ጽ/ቤቶች ይህንን ጉዳይ እንዲያጤኑ እና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች