ቅርንጫፍ ድጋፍን ያደረገው ከሰራተኞቹ ጋር በየአመቱ የሚያካደውን አመታዊ ክብረበዓል በመተው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ ሰባት የእለት ገቢ ለሌላቸው 70 ሰዎች ነው ፡፡
ድጋፉም 350 ሊትር ዘይት፣ 350 ኪ.ግ መኮሮኒ እና 140 ኪ.ግ ፓስታ ነው፡፡
በማዕድ ማጋራት መረሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አየለ ግርማ ባረጉት ንግግር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር በእንዲህ አይነት በጎ ምግባር ላይ በመሳተፍ በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጸው ባለስልጣኑ በሚሰጠው አገልግሎት መደገፍ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
በባለስልጣኑ የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ አርጋው በበኩላቸው ድጋፉን በማስተባበር ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከተው የቅርንጫፍ ባለራዕይ ሰራተኞች ማህበር እና የወረዳው አመራሮችን አመስግነዋል፡፡
አቶ ዮሴፍ ድጋፉ የቀናት ችግርን የሚቀርፍ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንደማይሆን ገልጸው አብሮነትን ለማሳየት የተደረገ በተቻለ መጠን ለወደፊትም መሰል ተግባባር ለማከናወን የሚያነሳሳ ነብለዋል፡የድጋፉ ተቀባዮችም ለተደረገላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡