በመረሀግብሩ ላይ በውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት እንዲሁም የቅርንጫፉ የፎረም አባላት የስራ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ወቅት ቅ/ጽ/ቤቱ ደንበኞቹ ዘንድ ከሚታዩ ችግሮች መካከል ከፍሳሽ ማሰባሰብ ጋር ተያይዞ ደንበኞች በተቀጠሩበት ቀን እና ሰዓት አለመገኘት ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነ ተመላክቷል ፡፡
በተለይ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ አገልግሎት የሚሰጥባቸው አካባቢዎች ለተሸከርካሪ በእጅጉ አስቸጋሪ ከመሆናቸው ጋር ተዳምሮ አገልግሎቱን ለመስጠት ወደ ስፍራው ሲኬድ ደንበኛው አለመገኘት ትልቅ ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡
ደንበኞች የተጠቀሙበትን የውሃ ፍጆታ ክፍያ በወቅቱ አለመክፈልም ሌላው እንደ ችግር የተነሳ ጉዳይ ሲሆን የደንበኞች ፎረም አባላት እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የደንበኞች ፎረም አባላቱ በበኩላቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ህዝቡን በማሳተፍ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
ከውሃ ስርጭት ጋር ተያይዞ አንድ አንድ ባለሞያዎች የውሃ ፈረቃን የማዛባት ችግር አለ ያሉት አባላቱ ቅርንጫፉ አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች