ባለሥልጣኑ በውሃ መገኛ አካባቢዎችን የተፋሰስ ልማት ስራ በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሰረት በመጪው የክረምት ወቅት ከ20 ሺህ በላይ የተለያዩ ችግኞች ለተከላ አዘጋጅቷል፡፡
በባለሥልጣኑ የተፋሰስ አስተዳደር እና ጥበቃ ዱቪዥን ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታዬ 15 ማሕበራት ያሉት በሰው ሃይል እና በመሳሪያ የተደራጀ የችግኝ ጣቢያ በማቋቋም የሐበሻ እና የፈረንጅ ጽድ፣ ሸውሸዌ፣ ብራዚሊያ፣ እና ግራር የመሳሰሉ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡
አቶ ሙሉጌታ አክለዉም የችግኝ ጣቢያው ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም ለችግኝ የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከማስቀረት ባሻገር ለአካባቢው ተወላጆች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል ብለዋል ፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች