ቀጣይ ሶስት ወራት የሚሰሩ እቅዶች በፍጥነት ፣በጥራት እና ችግር ፈቺ በሆነ መንገድ ለመተግበር ይቻል ዘንድ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ተብሏል ።በተለይ ደግሞ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዪ ችግሮችን መፍታት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ነው የተመላከተው ።በውይይቱ ላይ የየዘርፉ እቅድ የቀረበ ሲሆን በታቀደው ልክ ጊዜ የለኝም በሚል መንፈስ መፈጸም የሁሉም ሀላፊነት መሆን እንደሚገባ ተገልጿል።ተሳታፊ አመራሮችም እቅዶችን ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚሰሩ ገልጸው ባለስልጣኑ በተለይ ዋና ዋና ቦታዎች ላይ የሚታየውን የሰው ሀይል እጥረት መፍታት እንደሚገባው ገልጸዋል።