የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዛሬ የ6 ወራት የመደበኛ እና የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም በፕሮሰስ ካውንስል ገምግሟል ።
በግምገማው ወቅት ባለስልጣኑ ከገፀ ምድር እና ከርሰ ምድር የወሃ መገኛዎች አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ 94.2 ሚሊዮን ሜ. ኪ ወሃ አምርቶ ማስራጨት መቻሉ ተገልጿል ።
ይህም ከእቅዱ 82 % ሲሆን የእቅዱን ያክል ማሳካት ያልተቻለው በኤሌክትሮ ሜካኒካል ብልሽት፣ በኤሌትሪክ መቆራረጥ፣ ጉድጓዶች በጎርፍ መሞላት ዋነ ዋናዎች ችግሮች ናቸው ።
ገቢን ከመሰብሰብ አንፃር በ6 ወራት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሰበሰበ ሲሆን ይህም ከእቅዱ 96% ነው ።
ባለስልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ይቻል ዘንድ ለሠራተኞች እየተሠጣ ያለው ስልጠና (FLL ) በተጨባጭ በጣም ጥሩ ለውጥ እያመጣ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተገልጿል ።
ከስልጠና የወጡ ሠራተኞችም የተለያዩ የፈጠራ ስራ በመሰራት ተቋሙን አያገዙት አንደሆነ በማሳያ ቀርቧል ::
በውይይቱ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ
የተገኙ ጥሩ ውጤቶችን በማስቀጠል ፤ ክፍተቶችን ደግሞ ጠንክሮ በመሰራት ማሻሻል የሁሉም ሀላፊነት መሆኑ በመገንዘብ በትጋት መሰራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች