ባለስልጣኑ ከገፀ ምድር እና ከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች አለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ 140.3 ሚሊዮን ሜ. ኪ ውሃ አምርቶ ማስራጨት መቻሉ ተገልጿል ።

ከገጸ ምድር የውሃ መገኛዎች 55.75 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ እንዲሁም ከከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች 84.58 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማምረት ለነዋሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ተችሏል ፡፡

ይህም ከእቅዱ 85 % ያህል ሲሆን የእቅዱን ያክል ማሳካት ያልተቻለው በኤሌክትሮ ሜካኒካል ብልሽት፣ በኤሌትሪክ መቆራረጥ፣ ጉድጓዶች በጎርፍ መሞላት ዋና ዋናዎቹ ችግሮች ናቸው ።

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት ባጠቃላይ 213.97 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የገፀ-ምድር እና የከርሰ-ምድር ውሃን በማምረት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ፡፡