የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡት አራት የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች በኮልፌ ቀራኒዮ እና ጉለሌ ክ/ከ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በጥቅሉ በቀን 9ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችሉ ናቸው ፡፡
የፕሮጀክቶቹ በተዘረጉ መስመሮች ለተጠቃሚው እንዲደርሱ የተደረገ ሲሆን በተሰሩበት አካባቢ ፈረቃ እንዲሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመዲናዋን የውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት የባለስልጣኑ ቴክኒካል ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ደበበ ሙለታ በቀጣይም መሰል የከርሰ ምድር የውሃ ልማት ስራ ጎን ለጎን የገጸ-ምድር ውሃ ልማት ላይ በማተኮር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።
በምረቃው ላይ የተገኙ የአካባቢው ነዋሪዎችም በፕሮጀክቶቹ ግንባታ መደሰታቸውን ገልጸው ቀደም ሲል የነበረውን ችግር በከፊል እንደሚያቃልሉ አስረደረተዋል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኮልፌ ቀራኒዩ ፣ አዲስ ከተማና ጉለሌ ክ/ከ እና ወረዳ አመራሮች፣ የፎረም አባላት እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች