ቪትስ ኢቪድስ ዓለም አቀፍ የውሃ አማካሪ ድርጅት  በውሃ ብክነትና ቁጥጥር  ዙሪያ  ከዋና መ/ቤት እና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለተወጣጡ ባለሙያዎች  ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃ/ማርያም  እንደተናገሩት ተቋሙ በከፍተኛ ወጪ የገዛቸው የNRW መመርመሪያ ማሽኖች እስካሁን ድረስ በሚፈለገው ልክ ስራ ላይ አለመዋላቸውን ገልጸው፤ ባለስልጣኑ ለዚህም ችግር እንደ  ዋነኛ መንስኤ አድርጎ የለየው በመስኩ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች  የመሳሪያ አጠቃቀም ላይ ያላቸው የክህሎት ክፍተት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አቶ አወቀ አያይዘውም  ይህንን መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የክህሎት ክፍተቱን ለመሙላት ከፍተኛ አስተዋጾ ስለሚኖራቸው በቀጣይም  በተጠናከረ ሁኔታ እሰከ ውጭ ሀገር ድርስ በመላክ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡  ሰልጣኞችም  በስልጠናው ወቅት የሚቀስሙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ለውጥ ለማምጣት መስራት እንዳለባቸው ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡

ሚስተር ሄነስ ፐት የቪትስ ኢቪድስ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያ ስልጠናውን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት የተለያዩ ሀገራት መልካም ተሞክሮዎችን በስልጠናው ወቅት ማጋራታቸውን ገልጸው ሰልጣኞችም የNRW መፈተሻ መሳሪያዎች አጠቃቀምን በተግባር ስልጠና ተጨባጭ እውቅት እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ስልጠና ብቻ የተፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ስለማይቻል  በቀጣይም ተቋሙ ሌሎች ስልጠናዎችን በሚያዘጋጅበት ወቅት ማኔጀምንቱንም ታሳቢ  ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ከሰልጠኞች መካካል ከጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመጣችው ኢንጅነር ቲያ በላይ በሰጠችን አስተታያየት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተሰጠው ስልጠና በዙ አዳዲስ መሰረታዊ ነገሮች እንዳገኘችበትና በቀጣይም ለስራ አጋዥ እንደሚሆናት ገልጻለች፡፡  ሁሉም ሰልጣኞች ሌሎች መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡