የኘሮጀክቱ ሥም፡ አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ጥናት ፕሮጀክት
አስፈፃሚው አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት
ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ የሚያስችሉ አማራጭ የውኃ አቅርቦት ምንጭ በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡
የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- የከተማውን የወደፊት የውሃ ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ አማራጭ የውኃ አቅርቦት ምንጮችን በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- ነባርና አዳዲስ የሚገነቡ የውኃ ፕሮጀክቶች የሚሰሩበትን ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሌሎች አማራጭ ተጨማሪ የውኃ መገኛዎችን ማጥናት፣
ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-
- በ2007 ዓ.ም.
ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-
- በ2009 ዓ.ም.
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 106,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡
መግቢያ
ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን በመጠጥ ውሃ ችግር ውስጥ እየተዘፈቀ የሄደውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ችግር ለመቅረፍ መንግሥት የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ኘሮጀክቶችን ለመተግበር በርካታ የጥናት ሂደቶችን አጠናቋል፡፡ የጥናት ሂደቶቹ የከርሰምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሀብቶችን ማዕከል ያደረጉ ሲሆን በተለይ የከርሰ ምድር የውሃ መገኛ ጥናት የከተማውን የውሃ ፍላጐት በአጭር ጊዜ ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ለረዥም ጊዜ የከተማዋን የውኃ አቅርቦት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል ያስችል ዘንድ ከዚህ በፊት ከተጠኑ እና በመተግበር ላይ ከሚገኙ የውኃ መገኛዎች በተጨማሪ ሌሎች አማራጭ የውኃ መገኛዎችን በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ይህ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡
የሥራው አስፈላጊነት
ይህ ኘሮጀክት ተፈጻሚ ሲሆን የከተማዋን የረዥም ጊዜ የውኃ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ አማራጭ የውኃ መገኛዎች በመለየት ወደ ትግበራ እንዲገባበት የሚያስችል ይሆናል፡፡
የሥራው ዓላማ
የከተማውን የወደፊት የውሃ ፍላጎት ሊያሟላ የሚችሉ አማራጭ የውሃ መገኛዎችን በማጥናት ለትግበራ ማዘጋጀት ነው፡፡
የሥራው ግብ
የከተማውን የወደፊት የውሃ ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ አማራጭ የውኃ አቅርቦት ምንጮችን በማጥናት ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች
- የከተማዋን የረዥም ጊዜ የውኃ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አማራጭ የውኃ መገኛዎች ጥናት
በ2008 የሚከናወኑ ተግባራት
- ቀሪ 80 በመቶ አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ጥናት ሥራ ማከናወን
- የተቋራጭ ቅጥር ሂደት በመፈጸም አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ትግበራ ሥራ 15 በመቶ ማከናወን
- የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣
የአፈጻጸም ስልቶች
- የዝርዝር ጥናት ዲዛይን ሥራ የሚያከናውን አማካሪ መቅጠርና የጥናት ሥራውን መከታተል፤
ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች
- ዝርዝር ጥናቱን የሚያጠና አማካሪ የሚቀጠር ሲሆን አስፈላጊ ባለሙያዎችን በሙሉ አማካሪ ድርጅቱ ያቀርባል፡፡
የክትትልና የግምገማ ስርአት
- የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ለመከታተል ሳምንታዊና ወርሃዊ ሪፖርቶችን መከታተል፡፡
- የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት የዕቅዱን አፈፃፀም በየወሩ በመገምገም እቅዱን መከለስ
በጀት /ጠቅላላና ዝርዝር ወጪ/
ይህንን ሥራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው የማዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
34 | አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ጥናት እና ትግበራ ፕሮጀክት | 33,525,291 | 33,525,291 | 0 | 0 | 0 | ||
34.1 | አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ጥናት ሥራ ማከናወን | 3,906,614 | 3,125,291 | 3,125,291 | በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት ለጥናት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡ የጥናቱ ሥራ 4 ወር የሚፈጅ ነው፡፡ | |||
34.2 | አማራጭ የውሃ አቅርቦት ምንጭ ትግበራ ሥራ ማከናወን | 100,000,000 | 30,000,000 | 30,000,000 | ከትግበራ ሥራው ጋር በተያያዘ ለቅድመ ክፍያ የሚውል በጀት ነው፡፡ የትግበራ ሥራው 12 ወር እንደሚፈጅ ይጠበቃል፡፡ | |||
34.3 | የሱፐርቪዥን ሥራ ማከናወን | 1,200,000 | 400,000 | 400,000 | በሚገባው ውለታ መሠረት በወር 100ሺህ ብር ለመክፍል በ2008 በጀት ዓመት ለ4 ወር የሚከፍል በጀት ነው፡፡ |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች