የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለነዋሪዎች የሚያሰራጨውን ውሃ በፍታዊነት ለማዳረስ አንዱ የሆነውን የውሃ የግፊት ችግር ለመቅረፍ የዚሁ ሰለባ ከሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ጋር በመተባበር መስራት ጀምሯል ፡፡

በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በኦሎምፒያ ኮዶሚኒየም ሶስተኛ እና አራተኛ ወለል ነዋሪዎች እስከ 10ሺህ ሊትር የሚይዝ ሮቶ በመትከል እና ፓምፕ በማዘጋጀት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተዘረጋ መስመር እና ቴክኒካ ድጋፍ የረጅም ጊዜ ችግር መቅረፍ ተችሏል፡፡

ይቨው ተሞክሮ እንዲስፋፋ በስሩ ለሚገኙ 30 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተወጣጡ ተወካዮች ትላት አስጎብኝቷል ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት በኦሎምፒያ ኮዶሚኒየም 3ኛ ወለል ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ በላይነሽ ከበደ ከዚህ በፊት በፈረቃ ቢበጣም ፎቅ ላይ ስለማይደርስ ላላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት ይዳጋቸው እንደነበር ገልጸው ፤ አሁን በተሰራው ስራ ችግሩ መቀረፉን አብራርተዋል፡፡

በጉብኝቱ ተሳታፊ ከነበሩት ከጠብመንጃ ያዥ ኮዶሚኒየም ተወካይ የሆኑት ሻምበል ጳውሎስ ወ/ጊዮርጊስ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው በሚኖሩበት የጋራ መኖሪያ ቤት ተመሳሳይ ችግር ያለ በመሆኑ ባስልጣኑ በቀጣይ ለሚሰራው ስራ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ አስፋው በበኩላቸው ከዚህ በፊት ባለስልጣኑ አምርቶ የሚያሰራጫው ውሃ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከሦስተኛ ወለል በላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለው የውሃ ግፊት ችግር ለረጀም ጊዜ ነዋሪው ዘንድ ቅሬት ሲያሳማ መቆየቱን አንስተው ፤

ችግሩን ለመፍታት ከነዋሪዎቹ ጋር በመተባበር ይህ መፍትሄ ተበጅቷል የኦሎምፒያ የጋራ መኖሪያ ቤት በሞዴልነት የሚያገለግል ሲሆን መሰል ችግር ያለባቸው ቤቶች ተባብረው የሮቶ እና ፓምፕ ግዢ ካከናወኑ ቅርንጫፉ የመስመር ዝርጋታ እና ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ በስፋት እንዲሚሰራ ጠቁመዋል፡፡