የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባለፉት ዓመታት ለከተማው ነዋሪና ድርጅቶች ንፁህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ ዋነኛ ዓላማ አድርጎ ዘርፈ ብዙ የውኃ ልማት ሥራዎችን በማከናወን የከተማውን ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሥርጭት ለማሳደግ የተለያዩ ነባር እና አዳዲስ የከርሠ ምድርና የገፀ ምድር የውሃ መገኛ ምንጮችን በማልማት ለከተማዋ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃን ዘላቂና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማቅረብ ሰፊ የሆነ ሥራ ሰርቷል፡፡ ይሁንና የውሃ ምርት እጥረት አሁንም የዘርፉ ተግዳሮት ሆኖ መዝለቁን የውሃ ስርጭት እና ሲስተም ቁጥጥር የስራ ሂደት የሆኑት አቶ ታደሰ ይናገራሉ፡፡

ባለስልጣኑ ያለውን የውሃ ዕጥረት ከግምት ውስጥ በመስገባት ፍትሃዊ የውሃ ስርጭት እንዲኖር ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ጉድጓድ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ዕቅድ ነድፎ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅሰቃሴ ላይ ይገኛል በዚህም የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የራሳጨው ጉድጓግ ያላቸውን ተቋማት የመለየት ስራ ተሰርቷል፡፡ አቶ ታደሰ እንደገለጹት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር በተደረገው የዳሰሳ ጥናት …አገልግሎት የሚሠጡ 177ጎድጉዶች ያሏቸው 157 ተቋማት የተለዩ ሲሆን 16 ያህል ጉድጓዶች ደግሞ በኤሌክትሮ መካኒካል ብልሽት ምክኒያት የቆሙ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ እንደ አቶ ታደሰ ማብራሪያ 9 ያህል ጉድጓዶች  በውሃ ጥራት ችግርምክኒያት እንዲሁም 16 ያህል ጉድጓዶች በመንጠፍ ምክኒያት አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ተገልቷል፡፡

አቶ ታደሰ አያይዘውም ከፈተኛ ተቋማት የራሳቸውን ጉደጓግ በመጠቀም የውሃ አቅርቦቱ ላይ የሚያደርሱትን ጫና በመቀነስ የውሃ ስርጭቱ ፍትሃዊ ይሆን ዘንድ ጉድጓድ ላላቸውና ለወደፊቱም ለሚቆፍሩ ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ ከመስጠጥ ጀምሮ እስከማማከር የሚዘልቅ ድጋ ለመስጠት መታሰቡን እና የተለዩ ከፍተኛ የውሃ መጠን ተጠቃሚዎች የራሳችወ ጉድጓድ እንዲጠቀሙ የሚያበረታታ እና የሚያስገድድ የህግ ማዕቀፍ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡