የኘሮጀክቱ ሥም፡    የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ማስፋፊያ ኘሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ለገዳዲ ማጠሪያ ጣቢያ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የገፀ ምድርን ውሃ ሀብት በመጠቀም የአ.አ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ. እስከ 2015 በማጠናቀቅ በቀን ተጨማሪ 30,000 ሜ.ኪዩብ ውኃ በማምረት ወደ 272,727 የሚጠጋ የህብረተሰብ ክፍል የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 • የጥናትና ዲዛይን ሥራ
 • የDam intake ሥራ
 • የውኃ ማጣሪያ (Treatment Plant) ግንባታ ሥራ
 • የስርጭት መስመር (Transmition Pipe line work) ዝርጋታ ሥራ
 • የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥና ተከላ፣

 

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

 • በ 2001 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

 • በ2009 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 400,822,687 ብር የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

በከተማዋ ውስጥ የሚታየውን የመጠጥ ውሃ እጥረት ለማቃለል ይረዳ ዘንድ በተለያዩ ጊዜያት የተጠኑ የመነሻ ጥናቶች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ማስፋፊያ ኘሮጀክት ነው፡፡ የዚህን ኘሮጀክት ዝርዝር ጥናት በማጥናትና ወደ ተግባር በመለወጥ ተጨማሪ ውሃ ማግኘት የሚቻል ሲሆን በዚህም የሚታየውን የንፁህ ውሃ እጥረት በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ ያስችላል፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ በክረምቱ ወቅት ወደ ድሬ ግድብ ከሚገባው ውሃ ውስጥ ከግድቡ የመያዝ አቅም በላይ የሆነውንና በማስተንፈሻ ቦይ የሚወጣውን ውሃ ጥቅም ላይ ማዋል ሲሆን ለዚህም ተግባር የማስተንፈሻ ቦዩን ከፍታ በመጨመር የግድቡን የመያዝ አቅም መጨመርና ወደ ለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ የሚገባውን ውሃ መጠን ማሳደግ ይገኝበታል፡፡ በዚህም ተጨማሪ 30,000 m3 ውሃ በቀን ማምረት የሚቻልበትን የማስፋፊያ ሥራ ማከናወን ያስችላል፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

በአ.አ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ለማስወገድ እየደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅና ከሌሎቹ የአጣዳፊ ጊዜ ኘሮጀክቶች በተለይም የገፀ-ምድር ውሃ ሃብትን መሠረት ያደረገ በመሆኑ አስተማማኝነቱ ከሌሎቹ የተሻለ ኘሮጀክት ነው፡፡

ስለሆነም ከለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ የሚገኘውን አጠቃላየ የተጣራ ንፁሕ የመጠጥ ውሃ መጠን ከፍ የሚያደርገው ሲሆን ከዚህም ኘሮጀክቱ ቁጥሩ ከ 270,727 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኘሮጀክቱ ዓላማ

የማጣሪያ ተቋማት አቅምን በማሳደግና ካለ ጥቅም ይባክን የነበረውን የገፀ ምድር ውሃ በመጠቀም የከተማዋን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፤

የኘሮጀክቱ ግብ

የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በቀን ተጨማሪ 30,000 ሜ.ኪዩብ ውኃ በማምረት ወደ 272,727 የሚጠጋ የህብረተሰብ ክፍል የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

የሚጠበቅ ውጤት

 • በከተማዋ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ 272,727 በላይ የሆኑ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፣
 • ውሃ ለማፈላለግ የሚጠይቀውን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ምርታማነትን ያሳድጋል፣
 • በተበከለና ጥራቱ ባልተጠበቀ ውሃ የሚቸገረውን ህዝብ የጤና ዋስትና ባለው ውሃ ስለሚጠቀም ጤንነቱ የተጠበቀ ይሆናል፤
 • በከተማዋ ውስጥ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ያድጋል፤
 • የአ.አ ከተማን አለማቀፋዊነት እሴት ይበልጥ ያስቀብቃል፤

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

 • የለገዳዲ ግድብ ቀሪ የማሻሻያ ሥራ / Stage 2 Rehabilitation/ ማጠናቀቅ፣
 • ከኤሌክትሮክሎሪኔሽን ግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ የቴስት እና ኮሚሽኒንግ ሥራ ማከናወን፣
 • በመንግስት በጀት የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም እና ኤልሲ በማስከፍት የለገዳዲ ግድብ ስቶፕ ሎግ እና ድሬ ግድብ Bottom outlate ግንባታ ሥራ ማከናወን፣
 • የጨው መጋዘን ግንባታ ቀሪ ሥራ ማጠናቀቅ
 • የአማካሪ ቅጥር በመፈጸም የለገዳዲ ግድብ ስቶፕ ሎግ እና ድሬ ግድብ Bottom outlate የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማከናወን፣
 • የመያዥያ ክፍያ መፈጸም፣

የአፈጻጸም ስልቶች

 • በቀረበው ዝርዝር የመነሻ ጥናት መሠረት ጥራቱን የጠበቀና በአዳዲስ ቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋም መገንባት የሚያስችል የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት፣

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች

ይህ ኘሮጀክት ከአገር ውስጥና ከውጭ የተለያዩ ግብዓቶች የሚያስፈልጉት ሲሆን በተለይም፡-

 • የተለያዩ የማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ግብዓቶችና መለዋወጫዎች፣
 • ከፍተኛ የማስተላለፊያ ቧንቧዎችና መገጣጠሚያዎች፤

የአካባቢና የማሕበራዊ ትንታኔ

ይህ አካባቢ ለአዲስ አበባ ከተማ የመጠጥ ውሃ ዋና ምንጭ ሆኖ ለረዥም ዓመት እያገለገለ ያለ እንደመሆኑ መጠን የአካባቢውን ህብረተሰብ (ለገዳዲና ለገጣፎ ነዋሪዎች) ከለገዳዲ መስመር የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሳያደረግ ቆይቷል፡፡ አሁንም በልዩ ሁኔታ ትዕዛዝ ለአካባቢው ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ የሚያስችል ራሱን የቻለ ኘሮጀክት ተቀርጾ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርዓት

የኘሮጀክቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጥራቱን የጠበቀና ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን የተለያዩ የግምገማ ስርዓት ተዘርግቷል በዚሁ መሠረት የሚዘጋጁት የጥናት ሰነዶች እንደሁም የአገልግሎትም ሆነ የዕቃ ግዥ ሰነዶች ወደ አፈጻጸም ከመሄዳቸው በፊት በስፋት ግምገማና ምዘና የሚካሄድበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡

ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች

ኘሮጀክቱን ተግባራዊ ለማደረግ ያጋጥማሉ ተብለው የሚታሰቡ ስጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ስጋቶች

 • የባለቤትንት ጥያቄ ችግር (Right of Way)
 • የዓለም ባንክ የይሁንታ (No objection) የሚወስደው ጊዜ፣

ምቹ ሁኔታዎች

 • ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልገው በጀት በዓለመ ባንክ ዕርዳታ እንዲሁም ከመንግስት መገኘቱ
 • የህብረተሰቡ የውሃ ጥያቄ ከፍተኛ መሆኑ፤
 • የመንግሥትና የህብረተሰቡ ቁርጠኝነት፤

አጠቃላይና ዝርዝር በጀት

በ2008 በጀት ዓመት ሊሰሩ ለታቀዱ ሥራዎች የሚያስፈልገው በጀት 39,826,634 ብር ነው፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
8 የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት   39,826,634 39,826,634 0 0 0
8.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የለገዳዲ ግድብ ስቶፕ ሎግ እና ድሬ ግድብ bottom outlate ግንባታ ሥራ ማከናወን 29,826,000 20,000,000 20,000,000 በውሉ መሰረት 60 በመቶ ክፍያው ለውጭ ምንዛሪ የሚውል ሲሆን ከቀሪው ውስጥ ከመያዥያ ክፍያ ውጪ ያለው በ2008 በጀት ዓመት ለመክፍል ታቅዷል፡
8.2 የጨው መጋዘን ግንባታ ሥራ ማከናወን 2,274,309 1,819,448 1,819,448 በውሉ መሰረት በ2008 በጀት ዓመት የሚከፈል መያዥያ ክፍያ ነው፡፡
8.3 ከግንባታ ሥራው ጋር በተያያዘ የመያዥያ ክፍያ መፈጸም 588,496,005 10,313,186 10,313,186
8.4 ከሱፐርቪዥን ጋር በተያያዘ ቀሪ ክፍያ መፈጸም 41,888,832 2,694,000 2,694,000 በውሉ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ከዲፌክት ሊያቢሊቲ ሥራ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡
8.5 የለገዳዲ ግድብ ስቶፕ ሎግ እና የድሬ ግድብ bottom outlate ግንባታ ሥራ ጋር ተያይዞ የሱፐርቪዥን ክፍያ 10,000,000 5,000,000 5,000,000 ሥራው 10 ወር እንደሚቆይ እና በወር ለሱፐርቨዥን ሥራ 100ሺህ ብር እንደሚከፈል ታሳቢ በማድረግ በጀቱ ተይዟል፡፡