የአሰልጣኝ አመራረጥ ሂደትና መስፈርትን ማስፈፀም የወጣው መመሪያ ቁጥር 11/2011 ለአሰልጣኖች ፣ለሰልጣኞች ፣ ለስልጠና አስተባባሪዎች እና ለሌሎችም በስልጠናው ግብዓት ለሰጡ ባለሙያዎች የሚከፈለውን ክፍያ በአግባቡ ያልደነገገ የአከፋፈል ስርዓቱም ወጥና ተጠያቂነት የሰፈነበት የህዝብን ገንዘብ ከብክነትና ከምዝበራ የሚከላከል ባለመሆኑ ባለስልጣኑ ይህንን የስልጠና ሲሰጥም የአሰልጣኞች ምልመላም ሆነ የአሰልጣኞችና የተሳታፊዎች የክፍያ አፈፃፀም የሚመራበት ወጥ የሆነ መመመሪያ ባለመኖሩ ከውስጥ ሰራተኞች የአሠልጣኞች ምልመላ ሲያካሄድም ሆነ ከውጪ ሲጋብዝ ፣ የአሠልጣኞቹን ምርጫና ክፍያ አፈፃፀም እንዲሁም የሰልጣኞች አበል ክፍያን በሌላ አካል በወጣ መመሪያና በውስጥ አሠራር ላይ ተመስርቶ ሲያከናውን የቆየ በመሆኑ፤ይህንንም ክፍተት ለማስተካከል በማስፈለጉ፤
ባለስልጣኑ የሚሰጠውን ስልጠና መሰረት ያደረገ የአሰልጣኞች ምልመላ መስፈርትና የክፍያ ስርዓት በአግባቡ የሚደነግግ እና ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል የክፍያ ዘዴ እና የአመራረጥ መስፈረት በማዘጋጀት የስልጠና ስራዎችን በተገቢ ሁኔታ ለመምራት እንደሚረዳ በመታመኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3 (ሠ) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ረቂቅ ማሻሻያ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2020 አንቀፅ 7 መሰረት ማንኛውም የአስተዳደር መ/ቤት መመሪያ ከማውጣቱ በፊት ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላትና ከህዝብ የተሰበሰቡ አስተያየቶችንና በአስተዳደር ተቋሙ በአስተያየቶቹ ላይ የተወሰዱ አቋሞችን የያዘ መዝገብ ማደራጀት ያለበት ከመሆኑ በተጨማሪ በአዋጁ አንቀፅ 8 መሰረትም ማንኛውም የመንግስት መ/ቤት መመሪያ ከማውጣቱ በፊት በመመሪያው አወጣጥ ላይ የህዝብ ተሳታፊነትን ለማረጋገጥና የህብረተሰቡን አስተያየት ለማካተት ያመች ዘንድ ስለሚያወጣው ረቂቅ መመሪያ ሰፊ ስርጭት ባለው ጋዜጣ እና የተቋሙን ድረ ገጽ ጨምሮ በሌሎች የመገናኛ ብዙሃን የሚከተሉትን መረጃዎች የያዘ ማስታወቂያ ማውጣት ያለበት በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱም በዚህ አዋጅ አፈፃፀም ስር ከሚሸፈኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች አንዱ በመሆኑ ባለስልጣን መቤቱ ባዘጋጀው የአሰልጣኞች አመራረጥ መስፈርትና የአሰልጣኞችና የሰልጣኞች ክፍያ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ላይ የህዝብና የሚመለከታቸውን አካላት አስተያየት ለመሰብሰብ ያስችለው ዘንድ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል ፡፡ በመሆኑም የተዘጋጀውን ረቂቅ መመሪያ በድረ ገፃችን ላይ የጫንን በመሆኑ በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየቱን ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ለሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት በባለስልጣን መ/ቤቱ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት አስተያየቱን በፅሁፍም ሆነ በቃል ማቅረብ የሚችል መሆኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችል ሰውም አስተያየቱን በፅሁፍ በባለስልጣን መ/ቤቱ ድረ ገፅ ፣በባለሰልጣን መ/ቤቱ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1505 ወይም በአካል ለባለስልጣን መ/ቤቱ ህግና ኢንሹራንስ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 011 ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች