የፕሮጀክቱ ሥም፡ የመጋዘን ግንባታ ፕሮጀክት ቁ.4
አስፈፃሚው አካል፡ የአዲስ አባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ሳኒቴሽን ልማትና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡ በአዲስ አበባ ከተማ
የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡
- በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማቴሪያሎችና ማሽነሪዎች በአግባቡ ለማከማቸት፣
የፕሮጀክቱ ግብ፡
- የተለያዩ የተቋማት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች
- ለመጋዘን የዲዛይንና ቁጥጥር TOR ማዘጋጀት፣ ዲዛይን ማዘጋጀት፣
- የመጋዘን ግንባታ ጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት፣
- የ2 መጋዘን ግንባታ ማከናወን፣
የሚጠበቅ ውጤት፡
- በ2007/08 በጀት ዓመት የ3 መጋዘን ግንባታ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ንብረቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠር፡፡ በተጨማሪም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱን ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርጉትን የኪራይ መጋዘኖች ቁጥር መቀነስ ብሎም ማስቀረት
ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡
- በ 2007 በጀት ዓመት
ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡
- በ 2008 በጀት ዓመት
የፕሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት፡
- 19,000,000.00
መግቢያ
የፕ/ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ችግር በዘለቄታው ለመፍታት ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር በከፍተኛ መዋለ ንዋይ ዘመናዊና ጥራታቸውን የጠበቁ የውሃና የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቧንቧዎች የኤሌክትሮመካኒካል ዕቃዎችን በማስገባት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ንብረቶች ለግንባታ ወጪ እስከሚደረጉና የታሰበላቸውን የመጨረሻ ግብ ላይ እስከሚደርሱ ድረስ ጥራትና ይዘታቸው ሳይለወጥ ወይም ሳይበላሽ በአግባቡ እንዲቀመጡ ጥራቱንና ደረጃውን በጠበቀ መጋዘን/ማከማቻ ውስጥ መቀመጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት ፕ/ጽ/ቤቱ መሰል ተግባራት ለማከናወን የገዛቸውን ወደፊት በከፍተኛ መጠን የሚያስገባቸውን ዕቃዎች ለማስቀመጫ ከፍተኛ የመያዝ አቅም ያለው መጋዘን ለመገንባት ማቀዱ እጅግ መሠረታዊ የሆነ ሥራ ሲሆን በተጨማሪም ከዚህ በፊት በተገነቡ መጋዘኖች የመያዝ አቅም ማነስ የተነሣ የሚያጣውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ በማስቀረት ውጤት ያስገኝበታል፡፡
የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት
በከፍተኛ ገንዘብ ከውጭ ተገዝተው የሚገቡ የውሃና የፍሳሽ ቧንቧዎችና መገጣጠሚያዎች ፓምፕና የፓምፕ አክሰሰሪዎች በፀሐይና በዝናብ አልያም ባልተስተካከለ አቀማመጥ የሚኖርባቸውን ብልሽትና ብክነት ስለሚያስቀር አስፈላጊነቱ በጣም የጐላ ነው፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ
ፕሮጀክቱ በመጠንና በጥራት ደጃውን የጠበቀ መጋዘን በመገንባት መ/ቤቱ ለግንባታ የሚያስመጣቸውን የውሃና የፍሳሽ ዕቃዎች ምቹ ማስቀመጫ መፍጠር፣
የፕሮጀክቱ ግብ
የመጋዘን ግንባት ፕሮጀክት በ2007/08 በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ በበጀት ዓመቱ ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትን ከፍተኛ ንብረቶች በአግባቡ ለማስቀመጥ መቻል፡፡
የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች
በፕሮጀክቱ ግንባታ የሚጠበቀው ውጤት የንብረት መጋዘኑ በታሰበለት ጊዜና ፍጥነት እንዲሁም ጥራት ተጠናቆ የመጠጥ ውሃና የፍሳሽ ንብረቶች ሙሉ ለሙሉ ከአደጋ በራቀ መልኩ የሚከማቹበት ሁኔታ መፍጠር ሲሆን በግንባታው መንግሥትና ሕዝብ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
በ2008 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
- የ2 መጋዘን ግንባታ ቀሪ ሥራ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ
- ለነባር መጋዘኖች የመደርደሪያ እና የሼድ ግንባታ ሥራ ማከናወን፣
- የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ1 ተጨማሪ መጋዘን ከነመደርደሪያው ግንባታ ሥራ ማከናወን
- ግንባታቸው በ2008 በጀት ዓመት ለሚጠናቀቁ 2 መጋዘኖች የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የመደርደሪያ እና የሼድ ግንባታ ሥራ ማከናወን
የአፈጻጸም ስልቶች
የመጋዘን ግንባታ ፕሮጀክትን አፈጻጸም ለመቆጣጠር፡
- የዲዛይን TOR ማዘጋጀት፣
- በተዘጋጀው TOR መስፈርት መሠረት የሚቀርቡትን ተቋራጮች መገምገም፣
- የዲዛይን ሂደቱን በተዘጋጀው መስፈርት መገምገም፣
- የግንባታ ጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት ተቋራጮችን መገምገም፣
- ግንባታውን በቅርበት መከታተል የሚቀርቡትን ወቅታዊ ሪፖርቶች መፈተሽ የአፈጻጸም ስልቶች ሆነው ይተገበራሉ፡፡
ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የግንባታ ግበዓቶች
- ለግንባት የሚሆን የሲሚንቶ ውጤቶች፣
- ለግንባታ የሚሆኑ የብረት ውጤቶች እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣
- የሰለጠኑና ጥሩ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች /የግንባታ ባለሙያ/፣
- በቂ በጀት፣
የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ
- የፕሮጀክቱ መሰራት በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ጥሩ ማህበራዊ ኃይል ይኖረዋል፡፡
የክትትልና የግምገማ ስርዓት
የፕሮጀክቱ የዲዛይን እና የግንባታ ሥራ ዋና ዋና ተግባራት ሲኖሩት ሥራውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር በተዘጋጁት የTOR፣ የሳምንታዊና፣ ወርሃዊ ሪፖርቶች እንዲሁም ፕሮጀክቱ በሚገኙበት ቦታ የሚደረጉ የቁጥጥር ስርዓቶች ይዘረጋሉ፡፡
ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች
በፕሮጀክቱ ዋና ዋና፡
- ስጋት የሆኑ ጉዳዮች፡-
- የሲሚንቶና የግንባታ ግብዓቶች በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት፣
- ምቹ ሁኔታዎች፡-
- የመንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት፣
በጀት
- በበጀት ዓመቱ ከላይ የተገለፀውን መጋዘን ለማሰራት በአጠቃላይ 20,771,986 ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ዝርዝር ስርጭቱ እንደሚከተለው ይሆናል
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
29 | የመጋዘን ግንባታ ቁ.4 ፕሮጀክት | 20,771,986 | 20,771,986 | 0 | 0 | 0 | ||
29.1 | የ2 መጋዘን ግንባታ ሥራ ማከናወን | 8,464,983 | 6,771,986 | 6,771,986 | አጠቃላይ ሥራው በ2008 በጀት ዓመት በታህሳስ ወር የሚጠናቀቅ በመሆኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል አጠቃላይ ቀሪ ክፍያ በውሉ መሠረት የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
29.2 | ለነባር መጋዘኖች የመደርደሪያ እና የሼድ ግንባታ ሥራ ማከናወን፣ | 3,000,000 | 3,000,000 | 3,000,000 | በተገባው ውለታ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለአጠቃላይ የግንባታ ሥራው የተያዘ በጀት ሲሆን ሥራው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ | |||
29.3 | የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ1 ተጨማሪ መጋዘን ከነመደርደሪያው ግንባታ ሥራ ማከናወን | 4,300,000 | 8,000,000 | 8,000,000 | በ2008 በጀት ዓመት በሚገባው ውለታ መሠረት ከቀሪ 2.5 በመቶ የመያዥያ ክፍያ ውጪ ያለው ክፍያ በበጀት ዓመቱ ለመፈጸም ተይዟል፡፡ ሥራው የ6 ወር ሲሆን ከዚህ በፊት ከተገነቡት ተመሳሳይ መጋዘኖች በስፋት ይሄኛው በጣም ትልቅ እንደሚሆን ታሳቢ ተደርጓል፡፡ | |||
29.4 | ግንባታቸው በ2008 በጀት ዓመት ለሚጠናቀቁ 2 መጋዘኖች የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የመደርደሪያ እና የሼድ ግንባታ ሥራ ማከናወን | 3,000,000 | 3,000,000 | 3,000,000 | በሚገባው ውለታ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለአጠቃላይ የግንባታ ሥራው የተያዘ በጀት ሲሆን ሥራው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ሥራው የ3 ወር ነው፡፡ |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች