የኘሮጀክቱ ሥም፡ የቃሊቲ ፍሳሽ ተፋሰስ መለስተኛ ፍሳሽ መስመር ጥናትና ዝርጋታ ፕሮጀክት
አስፈፃሚው አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት
ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በቃሊቲ የፍሳሽ ተፋሰስ ውስጥ ለሚገኙ የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ አካባቢዎች
ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡-ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ያልተዳረሰባቸውን ቤቶችና በአካባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ከፍሎችን የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ ያስችል ዘንድ የነባር የቃሊቲ ፍሳሽ ተፋሰስ ጥናት መነሻ በማድረግ አዲስ የሚጠናቀቀውን የቃሊቲ ፍሳሽ መስመር በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል ዝርዝር የመጋቢ መስመር ጥናትና ዲዛይን ሥራ በማከናወን ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- የአማካሪ ቅጥር በመፈፀም የጥናት ሥራ ማከናወን
- የፍሳሽ ቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ መፈጸም
- የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ ማከናወን
ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-
- በ 2005 ዓ.ም.
ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-
- በ 2009 ዓ.ም.
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 1,000,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡
መግቢያ
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን እ.ኤ.አ. በ 2ዐዐ2 ዓ.ም የአዲስ አበባን ፍሣሽ ማስተር ኘላን ክለሳ ማስጠናቱ ይታወቃል፡፡ በተጠናው ማስተር ኘላን መሰረት የቃሊቲ ተፋሰስ ይገኝበታል፡፡ በማስተር ፕላን ጥናቱ መሰረት በየከተማዋ በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎች ከቤቶች ለሚለቀቁ ፍሣሾች የማስወገጃ መስመሮች እና አነስተኛ ማጣሪዎች አስፈላጊ ሆነው ስለተገኙ በ2ዐዐ5 የበጀት ዓመት በተመረጡ አካባቢዎች የፍሳሽ መስመር ጥናት የሚከናወን ይሆናል፡፡
የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት
በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎች በአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን የፍሳሽ ማስተር ኘላን ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች የፍሣሽ ማስወገጃ መስመሮችን በመዘርጋት የማስፋፊያ ስራ የሚሰራለት የቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ በተፋሰሱ ውስጥ የመለስተኛ መስመሮችን ስትራቲጅክ በሆነ መልኩ አጥንቶ መገንባት አስፈላጊ ይሆናል፡፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ
በርካታ የተፋሰሱ አካባቢዎች የፍሳሽ ማስወገጃ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የፍሳሽ መሰብሰቢያ መስመሮችን እንዲገነባ በማድረግ በአካባቢና በጤና ላይ የሚከሰተውን ችግር ማስቀረት ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ግብ
የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ላልሆኑ የተፋሰሱ አካባቢዎች መለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ በማከናወን በአካባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች
የጥናት ሲራው በበጀት አመቱ ተጠናቆ በቀጣይ ገንባታው ተግባራዊ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን በዚህም፡
- ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
- የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
- የአካባቢ ብክለትን ማስወገድና የተሟላ ጤና እንዲኖር ያደርጋል፡፡
- የፀዳች አዲስ አበባ እንድትኖረን ያደርጋል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት
- የቀሪ 73.3 ኪ.ሜ. የመለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ማከናወን፣
- የዕቃ አቅራቢ ቅጥር በማጠናቀቅ የማንሆል አቅርቦት ሥራ ማከናወን፣
- እስከ ሐምሌ መጨረሻ ኤልሲ በመክፍት እና የፍሳሽ ቧንቧና መገጣጠሚያ አቅርቦት በማከናወን ከ28 ኪ.ሜ. ውስጥ የ10.1 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ሥራ ማከናወን
- የወሰን ማስከበር ሥራ ማከናወን
- የግንባታ ቁጥጥር ሥራ ማካሄድ
የአፈጻጸም ስልቶች
- አማካሪ መምረጥና አማካሪው ጥናቱን እንዲያከናውን ማድረግ እና ሥራውን መከታተል፣
ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች
- ሥራውን የሚያጠና አማካሪ የሚመረጥ ሲሆን፣ አማካሪው የተጠየቀውን የሙያ አይነትና ባለሙያ በማቅረብ ጥናቱን ያከናውናል፡፡በፕሮጀክት ጽ/ቤቱም በኩልም እንዲሁ ሥራውን የሚከታተሉ መሃንዲሶች ይመደባሉ፡፡
የፕሮጀክቱ ግምገማ ሥርዓት
- ከአማካሪው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ጥናቱን በሚገመግሙ ባለሙያዎች እየታዩ መዳበር የሚገባቸው ነጥቦች እንዲዳብሩ ያደርጋል፡፡
ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች
ፕሮጀክቱ ተግባራው በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃሉ፡፡
ሀ/ ሥጋቶች
- ጥናቱን ለማከናዎን የሌሎች መሰረተ ልማቶችን መረጃ በጥልቀት ያለማግኘት ችግር
ለ/ ምቹ ሁኔታዎች
- ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድርግ የመንግስት ቁርጠኝነት፣
- በአካከባቢው ያለው የኢንቨስትመንትና ልማት መስፋፋት፣
- በአካባቢው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶችና ሌሎች ተቋማት፤ ዘመናዊ የፍሳሽ መሰብሰቢያ እና ማጣሪያ ኘላንት የሚፈልጉ መሆናቸው፣
- የነዋሪው ግንዛቤ እያደገ መምጣት፣
- ቀድሞ የተጠና የመነሻ ጥናት መኖር
- መረጀዎችን ለማሰባስብ ከሚመለከታቸው ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በጋራ መስራት መቻሉ
ከላይ ለተጠቀሱት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ በጀት 175,846,248 ብር ሲሆን ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
18 | የቃሊቲ ፍሳሽ ተፋሰስ መለስተኛ ፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት (ክፍል 10) | 175,846,248 | 175,846,248 | 0 | 0 | 0 | ||
18.1 | የ80 ኪ.ሚ የመለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ማከናወን | 108,593,978 | 50,000,000 | 50,000,000 | በ2007 በጀት አመት የቅድመ ክፍያ ብቻ እንደሚፈፀም ታሳቢ በማድረግ ቀሪ ከሚያዥያ ክፍያ ውጪ ያለው የበጀቱ መጠን ለቀጣይ የበጀት አመት እንዲያዝ ተደርጓል፡፡ ሥራው የ1 ዓመት ሲሆን ከሚያዝያ ጀምሮ ወደ ሥራ የተገባ ነው፡፡ | |||
18.2 | የአቅራቢ ቅጥር በመፈጸም ለፍሳሽ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግሉ የቧንቧ እና መገጣጠሚያ ግዥ መፈጸም | 20,229,559 | 0 | 0 | የዕቃ አቅርቦት ስራው በ2007 በጀት አመት ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ በመሆኑ ለቀጣይ የበጀት አመት በበጀት አልተደገፈም፡፡ | |||
18.3 | የ28 ኪ.ሜ የቧንቧና መገጣጠሚያ እና የዋና መስመር ዝርጋታ ስራ ማከናወን | 596,123,061 | 100,000,000 | 100,000,000 | በ2008 በጀት ከበጀቱ 40 በመቶ ለLC ማስከፈቻ እና 20 በመቶ ቅድመ ክፍያ እንዲሁም ከ10 ኪ.ሜ. ዝርጋታ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ክፍያ በጀቱ ተይዟል፡፡ ሥራው የ2 ዓመት በመሆኑ ቀሪው በጀት ወደ 2009 በጀት ዓመት ዞሯል፡፡ | |||
18.4 | የአቅራቢ ቅጥር በመፈጸም ለፍሳሽ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግሉ ማንሆሎች ግዥ መፈጸም | 19,428,180 | 15,000,000 | 15,000,000 | በ2008 በጀት ዓመት ለአቅርቦት ሥራው የሚከፈል በጀት ነው፡፡ | |||
18.5 | የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ | 1.381,629.55 | 846,248 | 846,248 | በ2007 በጀት አመት ለተቆጣጣሪ ድርጅቱ የ3 ወር ክፍያ እንደሚፈፀም ታሳቢ በማድረግ ከቀሪው ውስጥ ለቀጣይ 12 ወራት የሚከፈለው በጀት ለ2008 የበጀት አመት እንዲያዝ ተደርጓል፡፡ | |||
18.6 | የካሳ ክፍያ | 18,256,346 | 10,000,000 | 10,000,000 | ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች