የኘሮጀክቱ ሥም፡    የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን በቅርበት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፣

ግብ ፡- በአራዳ አካባቢ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማከናወን፣
  • የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት ግንባታ

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ 2006 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 50,000,00 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በአገልግሎት ቦታ ችግር ምክንያት የታሰበውን ውጤት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የአገልግሎት መስጫዎችን በመገንባት ችግሩን ለመፍታት ታቅዷል፡፡ የፕሮጀክቱ መተግበር የአገልግሎት ተጠቃሚው ህብረተሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ እና የባለሥልጣን መ/ቤቱን የቴክኒክ የማሰፈፀም አቅምን ከፍ እንዲል ያደርገዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

ይህ ፕሮጀክት የቅ/ጽ/ቤቱን አገልግሎትን በማቀላጠፍ የባለሥልጣን መ/ቤቱን የቴክኒክ ክፍል በማሳደግ በማጣሪያ ጣቢያ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት በኩል በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ

  • የቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገንባት ጥራቱን የጠበቀ የአገልግሎት መስጫ በማስገንባት ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት፣

የፕሮጀክቱ ግብ

በአራዳ አካባቢ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግንባታ በማከናወን የመ/ቤቱን ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

የሚጠበቁ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • የአካባቢው ሕብረተሰብ በቅርበት የተሟላ አገልግሎት ያገኛል፣
  • የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የማስፈፀም አቅሙን ይበልጥ ያሳድጋል፣
  • በየጊዜው ለቢሮ ኪራይ የሚወጣውን ገንዘብ በማስቀረት የመንግሥትን በጀት በአግባቡ ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • ቀሪ 50 በመቶ የጥናትና ዲዛይን ሥራ ማጠናቀቅ፣
  • ለግንባታ ሥራው የግንባታ ፍቃድ ማግኘት ሥራ፣
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም 25 በመቶ የቅ/ጽ/ቤት ግንባታ ሥራ ማከናወን፣

የአፈፃፀም ስልቶች

  • ቀጥተኛ የፕሮጀክት ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሥራዎች የዕለት ተዕለት ቁጥጥር ማካሄድ፣

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶች

  • ተቆጣጣሪ መሐንዲስ
  • ሲሚንቶና የሲሚንቶ ውጤቶች፣ የግንባታ ብረቶች፣ ማናቸውም ተጓዳኝ የግንባታ ግብአቶች፣
  • የስለጠነ ባለሙያ፣

የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ

የግንባታ ሥራዎች በሚገኙበት አካባቢ ለሚኖሩ አነስተኛና ጥቃቅን ድርጅቶች ለቀን ባለሙያዎችና ለአገር ውስጥ ከፍተኛና መለስተኛ ተቋራጮች ጥሩ የሥራ ዕድል ስለሚከፍት ጥሩ የማህበራዊ እሴት ይኖራቸዋል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርዓት

  • የፕሮጀክቶችን እንቅስቃስ ለመከታተል ሳምንታዊና ወራዊ የሳይት ሪፖርቶችን መከታተል፣
  • ወርሃዋ የፕሮጀክት ፕላን በማዘጋጀት ዕቅዱንና አፈፃፀሙን በየወሩ በመገምገም፣
  • የፕሮጀክቶዡን እንቅስቃሴ ዕቅድንና አፈፃፀሙን በማቀናጀት ለሚመለከተው አካል መላክ፣
  • የፕሮጀክቶች ዕቅድ ከፊዚካል አፈፃም ጋር አለመጣጣም ሲገኝ እቅዱን መከለስ፡፡

ሥጋትና ምቹ ሁኔታዎች

የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት ግንባታ በታሰበላቸው ግብ ለመሰራት የሚያጋጥሙ ዋና

ሥጋቶች

  • የግንባታ ግብአቶች በበቂ ሁኔታና በታሰበ ጊዜ አለመገኘት፣
  • የግንባታ ግብአቶች ዋጋ መጨመር፣
  • በቂ የሰለጠነ ባለሙያ አለማግኘት፣
  • የግንባታ ቦታ በወቅቱ አለማግኘት

  ምቹ ሁኔታ

  • መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት
  • ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በባለሙያዎች ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት በሙሉ አቅማቸው መትጋት፣

የ2008 በጀት ዓመት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ በጀት 20,496,310 ሲሆን ይህ በጀት ከዚህ በፊት ባለሥልጣን መ/ቤቱ ያሰራቸውን ቅ/ጽ/ቤቶች መነሻ ዋጋ እና አሁን ያለውን ወቅታዊ ዋጋ መነሻ በማድረግ የተያዘ ነው፡፡

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
26 የአራዳ ቅ/ጽ/ቤት ጥናት እና ግንባታ ፕሮጀክት   20,496,310 20,496,310 0 0 0
26.1 የዲዛይን ጥናት ማከናወን 22,000 17,600 17,600 በ2007 በጀት አመት የዲዛይን ዝግጅቱ 50 በመቶ የሚጠናቀቅ በመሆኑ እና በቀጣዩ  ማለትም 2008 የበጀት አመት ቀሪው 50 በመቶ ስራው እስከ ሐምሌ ወር  የሚጠናቀቅ በመሆኑ ለቀሪ ክፍያው በውሉ መሠረት የተያዘ በጀት ነው፡፡
26.2 የተቋራጭ ቅጥር በመፈፀም የንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት  ግንባታ ማከናወን 48,000,000 20,300,000 20,300,000 በበጀት ዓመቱ በሚገባው ውለታ መሠረት የቅድመ ክፍያ 20 በመቶ እና የግንባታውን 25  በመቶ የሚከናወን በመሆኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለሚከፈል ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡ ( ስራው ለ18 ወራት እንደሚከናወን ታሳቢ ተደርጓል፡፡)
26.3 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ 459,540 178,710 178,710 በውል ስምምነቱ መሠረት በየወሩ ለሚያካሄደው የሱፐርቪዥን ሥራ በየወሩ የሚከፍል ሲሆን በዚህ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ4 ወር በየወሩ ክፍያ ለመፈጸም የተያዘ በጀት ነው፡፤