የኘሮጀክቱ ሥም፡    የአያት ዌልፊልድ ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ ልማት ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-      በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-በኦሮሚያ ከተሞች (አያት አካባቢ) ነው

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የአዲስ አበባ ከተማን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በማሳደግ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡-አሁን ያለውን የከተማዋን የመጠጥ ውኃ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ የጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና  የመስመር ዝርጋታ ሥራ በማጠናቀቅ የከተማዋ ህብረተሰብ የንፁ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የሃይድሮሎጂካል እና የጂኦፊዚካል ጥናት፣
  • ጥልቅ የሙከራና ምርት ጉድጓዶች ቁፋሮና ፓምፕ ቴስት ሥራ፣
  • የውኃ ማስተላለፊያ መስመር ኔትወርክ፣ ማጠራቀሚያ ጋንና የግፊት መስጫ ጣቢያ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ጥናት ማካሄድ
  • የስርጭት (Transmission Line) መስመር እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ጥናት ማካሄድ፣
  • የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች የዕቃ ግዥና ግንባታ፣
  • የቧንቧና መገጣጠሚያ ግዥ፣
  • ለተቆፈሩ ጉድጓዶች ወደ ማጠራቀሚያ ጋኖች መሰብሰቢያ (Collector pipes)  የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
  • የማጠራቀሚያ ጋን እና ሌሎች አስፈላጊ የህንጻ ግንባታ ሥራዎች
  • የዋና መስመር ዝርጋታ ሥራ፣
  • የፓምፕና ጥበቃ ቤት ግንባታ እንዲሁም የትራንስፎርመር ተከላ ሥራ
  • ከጉድጓድ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ የካሳ ክፍያ
  • የግንባታ ሱፐርቪዥን ሥራ

 

ከኘሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት

  • ይህ ኘሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የከተማዋ ህዝብ የንፁ መጠጥ ውኃ አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

  • በ2007 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ2010 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት

  • ከ1.5 ቢሊየን ብር በላይ ይፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

 ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን በመጠጥ ውሃ ችግር ውስጥ እየተዘፈቀ የሄደውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ችግር ለመቅረፍ መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ኘሮጀክቶችን ለመተግበር በርካታ የጥናት ሂደቶችን አጠናቋል፡፡ የጥናት ሂደቶቹ የከርሰምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሀብቶችን ማዕከል ያደረጉ ሲሆን በተለይ የከርሰ ምድር የውሃ መገኛ ጥናት የከተማውን የውሃ ፍላጐት በአጭር ጊዜ ከመፍታት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

ኘሮጀክት ጽ/ቤቱ የሚያስቆፍረው ይህ ሥራ የጽ/ቤቱን የማስፈፀም አቅም በሰው ኃይል በማሳደግ እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡ ይህ ተግባር በውስጥ የዘርፍ ተቋማት፣ የሚከሰተውን ችግር በመቅረፍ ጥልቅ ጉድጓዶች የሚገኘውን አነስተኛ ምርትና በየጊዜው የሚከሰተውን የውሃ ምርት መጠን በማስወገድ ከፍተኛ ውጤት ይሰጣል፡፡

የኘሮጀክቱ አስፈላጊነት

 በአፍሪካ መድረክ ከፍተኛ የፖለቲካ ሚና ያላት አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄን ለመመለስ ሳትችል ለበርካታ ጊዜ ቆይታለች፡፡ በቅርብ የተደረጉ አንዳንዱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከተወሰኑት የከተማው አካባቢዎች በስተቀር በአዲስ አበባ የ24 ሰዓት የውሃ ሽፋን የሚያገኙ አካባቢ እጅግ ውስን ከመሆናቸውም በላይ ችግሩ ይበልጥ በተጠናከረባቸው በፈረንሣይና በአስኮ አካባቢዎች በ15 ቀን ፈረቃ የቧንቧ ውሃ የሚሰራጭበት አካባቢ እንዳለ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም ይህ በከተማው ዙሪያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚቆፈር ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ ኘሮጀክት ተጨማሪ ውኃ በማግኘት ለአገልግሎት ዝግጁ የሚያደርግ ሲሆን ግምቱ ከፍተኛ የሆነ የከተማዋ ህዝብ የ24 ሰዓት የተሟላ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡

 የኘሮጀክቱ ዓላማ

 በጥልቅ ጉድጓድ ያለውን የእስከአሁን ተሞክሮ በማሳደግና ከአንድ ጉድጓድ የሚገኘውን ምርት በመጨመር የከተማውን የውሃ ፍላጐት በአጭር ጊዜ ማሟላት፣

የኘሮጀክቱ ግብ

 ጥልቅ ጉድጓዶችን በመቆፈርና የመስመር ዝርጋታ ሥራ በማከናወን ተጨማሪ ውኃ በማምረት ግምቱ ከፍተኛ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል የአገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ይህ ኘሮጀክት በሂደት ላይ እያለና በአጠቃላይ ሥራው ሲጠናቀቅ ለከፍተኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ በቀጥተኛና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

በኘሮጀክቱ ሂደት የሚጠበቁ ውጤቶችና ተጠቃሚዎች መካከል

  • በኘሮጀክቱ አካባቢ ለሚገኙ በርካታ የከተማ ነዋሪዎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል ይከፍታል፣
  • በተከለሉ የውሃ መገኛ ቦታዎች የሚቆፈሩት እነዚህ ጉድጓዶች በከፍተኛ ጥልቀት የሚቆፈሩ ስለሆነ በዘርፉ ያለውን ተሞክሮ ይበልጥ ያጠናክራል፡፡
  • በኘሮጀክት ቢሮው በራስ አቅም የሚሰሩ ስራዎች ለተወሰኑ ባለሙያዎች ከፍተኛ የሥራ ልምድ ይፈጥራሉ፡፡

ከኘሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላ የሚገኙ ውጤቶችና ጥቅሞች

  • በከተማው የሚገኘው ከፍተኛ የሆ የህብረተሰብ ክፍል ንፁህ ውሃ ያገኛል፣
  • ውሃ ለመፈለግ የሚጠይቀውን ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ ምርታማነትን ይጨምራል
  • በተበከለና ጥራቱን ባልጠበቀ ውሃ የሚቸገረው ህዝብ ጥሩ የጤና ዋስትና ባለው ውሃ ስለሚጠቀም ጤንነቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  • በከተማው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በይበልጥ ያሳድጋል፣
  • የከተማው ህዝብ ከመንግሥት ጋር አብሮ በጋራ በመስራት መልካም አስተዳደርን ይበልጥ ያሳድጋል፡፡
  • የአ/አ ከተማን አለምአቀፋዊ እሴት ይበልጥ ያስጠብቀል፡፡

በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት

  • በዌል ፊልዱ ከሚቆፈሩ 15 የምርት ጉድጓዶች ውስጥ የቀሪ 11 ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ማጠናቀቅ፣
  • የኤሌክትሮሜካኒካል፣ የዋና እና የማሰባሰቢያ እንዲሁም የሲቪል ሥራዎች ጥናትና ዲዛይን ሥራ ቀሪ 80 በመቶ ማከናወን፣
  • ለኤሌክትሮሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ፣ የዋና እና የማሰባሰቢያ መስመር ዕቃ አቅርቦትና ዝርጋታ እንዲሁም ተያያዥ የሲቪል ሥራዎች የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የሞቢላይዜሽን ሥራ ማከናወን
  • የወሰን ማስከበር ሥራ ማከናወን፣

የአፈጻጸም ስልቶች

  • በአዲስ አበባ ገጠር አካባቢዎችና በአጐራባች የኦሮሚያ ቀበሌዎች ለውሃ መገኛ የሚሆኑ አካባቢዎችን መለየትና የውሃውን ጥራትና የአካባቢውን ምርታማነት የሚቀንሱ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች መቆጣጠር፣
  • በተመረጡ ቦታዎች የጂኦፊዚካል ጥናቶችን ማስጠናት ዝርዝር የጉድጓድ ዲዛይን ማሰራት፣
  • በተቋራጭ ድርጅቶች ለሚያስቆፍራቸው ጉድጓዶች
    • የግንባታ የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት ጨረታ ማውጣትና ግንባታ ማካሄድ፣
    • በተዘጋጀው ዲዛይን ስራው መከናወኑን መቆጣጠር፣
  • ለተቆፈሩት ጉድጓዶች የሚሆኑ ፓምፖችና ቧንቧዎችን ማጠራቀሚያ ጋኖችን መግዛት፣
  • አዲስ የተገነቡትን ጉድጓደች ከነባር ሲስተም ጋር በማጣጣም የግፊትና የመመለሻ መስመር ጥናትና ዲዛይን ማሰራት ግንባታ ማከናወን እና ቁጥጥር ማካሄድ፣

ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች

ይህ ኘሮጀክት ከአገር ውስጥና ከውጭ የሚገኙ በርካታ ግብአቶችን የሚያስፈልጉት ሲሆን በተለይ፡-

  1. ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የተሻለ ሙያና የሥራ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ማዘጋጀት፣
  2. ከፍተኛ የመግፋትና የመሣብ ኃይል ያለው ፓምኘና መገጣጠሚያዎች፣
  3. ከፍተኛ የግፊትና የመመለሻ መስመር ቧንቧዎችና መገጣጠሚያዎች፣ ማጠራቀሚያ ጋኖችና ተጓዳኝ የግንባታ ዕቃዎች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ተገዝተው ለኘሮጀክቱ ግብዓት መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

የአካባቢና የማህበራዊ ትንታኔ

የአዲስ አበባን የውሃ ችግር ለመቅረፍ አይነተኛ መፍትሄ ተብሎ የተቀመጠው ይህ ኘሮጀክት ከታሰበበት ዋና አገልግሎት በተጨማሪ የውሃ መገኛ አካባቢ የሚገኙትን ሕብረተሰቦችን ያማከለ ስለሆነ መልካም የአካባቢና ማህበራዊ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

በግባታ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉትን የይዞታ ጥያቄና የካሣ አከፋፈል ችግሮችን ሕብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እንዲሰራ የታቀደ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪ ከሚገኘው ውሃ የቅድመ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

የክትትልና ግምገማ ስርዓት

የኘሮጀክቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ጥራቱን የጠበቀና ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን የተለያዩ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት የተዘረጋ ሲሆን ከዚህም አንዱ ለራሱ የሆነ አማካሪ በመቅጠር የሱፐርቪዥን ሥራው በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ሥጋትና ምቹ ሁኔታዎች

የሚከተሉት ነጥቦች ኘሮጀክቱ ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የሚያጋጥሙና ምቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

  1. ስጋቶች
    • ከውጭ ተገዝተው የሚመጡ የኤሌክትሮመካኒካል ዕቃዎች የአቅርቦት ችግር፣
    • በከፍተኛ ጥልቅ ቁፋሮ የተሰማሩ ተቋራጮች የአቅምና ብሎም በብዛት ያለመገኘት ችግር፣
    • የወሰንና የ ‘right of way’ ችግር
  2. ምቹ ሁኔታዎች
    • ኘሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ የመንግሥት ቁርጠኝነት፣
    • የሕብረተሰቡ የውሃ ጥያቄ ከፍተኛ መሆኑ፣
    • በከተማው ያለው የኢንቨስትመንትና ተጓዳኝ ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች፣
    • የአዲስ አበባ አለም አቀፋዊ እሴት፣
    • የፍላጐትና የአቅርቦት አለመጣጣምና የከተማው አስተዳደር ከፍተኛ ድጋፍ፣
    • የህብረተሰቡ ጥያቄ፣

አጠቃላይ እና ዝርዝር በጀት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
3 የNorth Fanta Ayat ዌልፊልድ ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ ልማት ፕሮጀክት   75,244,495 75,244,495 0 0 0
3.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ15 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ማከናወን 112,045,247 40,000,000 40,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለ2008 ለሚሰሩ ሥራዎች የተያዘ በጀትነው፡፡
3.2 የኤሌክትሮሜካኒካል፣ የዋና እና የማሰባሰቢያ እንዲሁም የሲቪል ሥራዎች ጥናትና ዲዛይን ሥራ  ማከናወን 4,884,395 4,151,735 4,151,735 በተገባው ውለታ መሠረት ጥናቱ የ7 ወር ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት የጥናቱ ኢንሰምሽን ሪፖርት ብቻ የሚቀርብ በመሆኑ ከዚህ በተያያዘ መከፍል ያለበት በጀት ተይዟል፡፡ ቀሪው በጀት ወደ 2008 ተዘዋውሯል፡፡
3.3 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ፣ የዋና እና የማሰባሰቢያ መስመር ዕቃ አቅርቦትና ዝርጋታ እንዲሁም ተያያዥ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 11 በመቶ ማከናወን 1,500,000,000 25,000,000 25,000,000 በሚገባው ውለታ መሠረት ለ2008 ለሚሰሩ ሥራዎች ቅድመ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡
3.4 ለሲቪል ሥራ የሱፐርቪዥን ክፍያ ሥራ 5,071,040 1,267,760 1,267,760 በተገባው ውለታ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት ለ3 ወር የግንባታ ቁጥጥር ሥራ የተያዘ በጀት ነው፡፡
3.5 የካሳ ክፍያ መፈጸም 4,825,000 4,825,000 4,825,000 ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘ ለሚከፍል ካሳ ክፍያ የተያዘ በጀት ነው፡፡