“ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል የባለሥልጣኑ ሰራተኞች የሀገር መከላከያ ሰራዊታን ለመደገፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር በመካኒሳ ቅ/ጽ/ቤትና በዋናው መ/ቤት አከናውነዋል።
በደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ላይ አስተባባሪ የሆኑት የባለሥልጣኑ የሴቶች ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ኤጀርሳ የደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ዓላማ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ህግ በማስከበር ተግባር ላይ ለተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ደም የለገሱት የባለሥልጣኑ ሰራተኞችም በበኩላቸው “መከላከያ ሰራዊታችን የሀገር ሉዋላዊነት መረጋገጥ አለኝታ እና መከታ ስለሆነ በምንችለው ነገር ሁሉ ከጎኑ እንቆማለን።” ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።
የአዲስአበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም መለገስ ብቻ ሳይሆን የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች 14.4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።