በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ እና የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመውባቸው በማገገም ላይ ላሉ 60 ሴቶች 15 ሺህ ብር የሚያወጣ የሩዝና የፖስታ ድጋፍ ተደርጓል ።
ድጋፉን ያስረከቡት በባለሥልጣኑ የቦርድና ስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት መሠረት አሰፋ በቀጣይም ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግና ከጎናችሁ ለመሆን ዝግጁ ነን ብለዋል።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዘንድሮ በዓለም ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ “የሴቶችን መብት የሚያከብር ህብረተሰብ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል።