በአዲስአበባ የስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ለ12ኛ ጊዜ በከተማ ደረጃ ከጥር 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ስፖርቶች ውድድር ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል።በዚህም ውድድር ባለሥልጣን መ/ቤቱ በተሳተፈባቸው የመረብ ኳስ እና የእግር ኳስ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን ዋንጫ አንስቷል።በዛሬው የመዝጊያ ውድድር የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገው የእግር ኳስ ቡድን የሸገር ብዙኃን ትራንስፖርትን 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ዋንጫውን ማንሳት የቻለው።በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይም ከባለስልጣኑ ስፖርት ቡድን _አቶ አንዋር ከድር በእግር ኳስ ምርጥ አሰልጣኝ፣_ አብዱረህማን በርጋ በእግር ኳስ ኮኮብ ተጫዋች እንዲሁም_ ፈዴሳ ያደቹ በመረብ ኳስ ኮኮብ ተጫዋች በመሆን ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።