ቋሚ ኮሚቴው የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክት ፣ የቦሌ አራብሳ ፣ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ፣ የቦሌ ቡልቡላ እና ሪፌንቴ አካባቢ እየታሰሩ ያሉ የውሃ እና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ምልከታ አድርገዋል።የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢው የተከበሩ ወ/ሮ ልእልቲ ግደይ ባለስልጣኑ በተለይ የህዝብ ቅሬታ የሚነሳባቸውን ቦታዎች በመለየት አፋጣኝ መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።በተለይ መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በልዩ ትኩረት እና ፍጥነት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።