የለገዳዲ ገፈርሳ እና ድሬ ግድቦችም ልዩ ጥበቃ እና ክብካቤ ከሚፈልጉ ፕሮጀክቶች መካከል መናቸውን ተከትሎ ባለስልጣኑ በግድቦች ዙሪያ እና በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ዙሪያ ከ5000 በላይ ችግኞች በመትከል እየተንከባከበ ይገኛል ፡፡
በባለስልጣኑ የተፋሰስ አስተዳደር ቁጥጥር እና ልማት ባለሞያ አቶ አደም መጎስ ችግኞቹ ለመንከባከብ ይመች ዘንድ 19 ሰራተኞች በኮንትራት በመቅጠር የክብካቤ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል ፡፡
ችግኞቹም መሬት ተሸርሽሮ ግድቦቹ በደለል እንዳይሞሉ ከመከላከል ባሻገር የአካባቢውን ስነ ምህዳር በመጠበቅ ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች