ደንበኞች ቅጥያ ለማሰራት የሚያስችላቸውን መስመር መዘርጋትን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን ያደረገ ሲሆን በቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ተፋሰስ ስር የሚገኙ እና መስመር የተዘረጋባቸው አካባቢዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባለስልጣኑ ያሳውቃል፡፡

ከዚህም ጎን ለጎን ባለስልጣኑ የዘመናዊ ፍሳሽ ደንበኞቹን የቤት ለቤት ቆጠራም አካሂዷል ፡፡
ቆጠራው በዋናነት የፍሳሽ በመስመር ተጠቃሚ ደንበኞችን የሚመለከት ሲሆን አጠቃላይ ከአንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ (167000) በላይ ደንበኞች እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከእነዚህም 92 በመቶ የመኖሪያ ቤቶች ሲሆኑ ቀሪ 8 በመቶ ደግሞ የንግድ ተቋማት ናቸው፡፡

ቆጠራውም በከተማዋ ውስጥ የዘመናዊ ፍሳሽ ቆሻሻ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑና ያልሆኑትን በመለየት ተጨማሪ ፕሮጀክችን ለመቅረጽ የሚያስችል ሲሆን ለተለያዩ ጥናቶችና የፕሮጀክት ስራዎች እንደመነሻ ሆኖም ያገለግላል፡፡