በባለሥልጣኑ ውሃውን ከብክነት ያዳነው፡- ያረጁ መለስተኛ እና ከፍተኛ የውሃ መስመሮችን በመቀየር፣ ተከታታይነት ያለው መደበኛ የውሃ ብክነት ምርመራ እና ቁጥጥር ስራ በተለያዩ መሳሪያዎች በማከናወን ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ቅርንጫፎች የሚገባውን እና የሚወጣውን የውሃ መጠን ለመቆጣጠር ከፍተኛ እና በመለስተኛ መስመር ላይ 53 የውሃ ቆጣሪዎችን በመትከል እንዲሁም ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ቆጣሪዎች በመቀየር እና ሌሎች ተግባራትን በማከናወን የውሃ ብክነቱን መከላከል መቻሉን በባለስልጣኑ ገቢ የማይሰበሰብበት ውሃ ክትትል፣ ቁጥጥር እና አስተዳደር የስራ ሂደት ተወካይ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ባለሥልጣኑ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ከብክነት ለመከላከል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመደገፍ ረገድ ህብረተሰቡ ውሃ እየፈሰሰ ነው ጥቆማዎችን በመስጠት የሚያደርገው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ሀብታሙ ይቨው ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላፈዋል ፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች