የባለስልጣኑ ሠራተኞች ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን 14 ሚሊየን 463 ሺህ 815 ብር ለግሰዋል፡፡
ድጋፉን ያደረጉት በዋናው መስሪያ ቤት እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ ቋሚ እና ኮንትራት ሠራተኞች መሆናቸውን በባለስልጣኑ የፋይናንስ ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ ወ/ሮ ላቀች አግደው አስታውቀዋል፡፡
ከተጠቀሰው ድጋፍ በተጨማሪም በባለስልጣኑ ስፖርት ኮሚቴ አማካኝነት ሠራተኛው ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በየወሩ ከሚያዋጣው ገንዘብ የ5 ወር መዋጮውን 200 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን የኮሚቴው ምክትል ሠብሳቢ አቶ ወርቁ አንዷለም ገልፀዋል፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች