ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት በዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት አራዳ፣ ጉለሌ፣አዲስ ከተማ እና መገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
የጥር ወር እና በያዝነው የካቲት ወር በቀሪ ሌሎች አራት የቅ/ጽ/ቤቶች ማለትም ጉርድ ሾላ ፣መካኒሳ ፣ንፋስ ስልክ እና አቃቂ ቅ/ጽ/ቤቶች ስር በሚገኙ ደንበኞች ላይ ተግባዊ ተደርጓል፡፡
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ስር የሚገኙ ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን ለመግለጽ ያክል፡-
ጉርድ ሾላ ቅ/ጽ/ቤት ፡-ቦሌ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 6 እሰከ 14፣የካ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 10 እሰከ 13
መካኒሳ ቅ/ጽ/ቤት ፡- ኮልፌ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እሰከ 9፣ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 እና 10 ፣ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ከወረደ 1 እስከ 4 እና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ 5 (በከፊል)፣ 6፣ 7፣ 10 እና 11
ንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት ፡-ንፋስ ስልክ ክፈለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 12 ፣ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እሰከ 9 እና አቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6
አቃቂ ቅ/ጽ/ቤት ፡- ከወረዳ 6 በስተቀር ሁሉንም ወረዳዎች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ እና የመንግስት ተቋማት ሌሎችም የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከ26 እስከ 18/2012 ዓ.ም በየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በተዘረጉ የተለያዩ የክፍያ አማራጮች የጥር እና የካቲት ወር የውሃ አገልግሎት ክፍያ እንደሚፈጽሙ በመረዳት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ ያሳስባል ፡፡
በዚህ የዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት በአጠቃላይ በከተማዋ የሚገኙ 560 ሺ በላይ የውሃ ደንበኞች ከየካቲት 26 ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀመጡ አማራጮች መክፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች