በዚህ ወር ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ የተደረገባቸው አራዳ፣ ጉለሌ እና መገናኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሲሆኑ ፡-

በጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስር ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 8 ፣ አራዳ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 እስከ 7፣ የካ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 4 የሚገኙ ከ55,000 በላይ ደንበኞች ፤

አዲስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ስር ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9እና 10፣ አዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 4፣5፣6፣7፣9፣እና 10፣ ኮልፌ ክ/ከ ከወረዳ 6 እስከ 15 ሲሆን ወረዳ 9 በከፊል ፤ እንዲሁም ልደታ ክ/ከ ወረዳ 2 በድምሩ 57,823 ደንበኞች፤

መገናኛ ቅ/ጽ/ቤት ስር፡ -የካ ክ/ከተማ ወረዳ 5፣7፣8 ፤ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 1፣5፣12 ፣ 13 በከፊል፤ ቂርቆስ ወረዳ 1 በከፊል በድምሩ 38,605 ደንበኞች ናቸው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ቅርንጫፍ ስር የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ እና የመንግስት ተቋማት ሌሎችም የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከ26 እስከ 18/2012 ዓ.ም በየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በተዘረጉ የተለያዩ የክፍያ አማራጮች የታህሳስ እና የጥር ወር የውሃ አገልግሎት ክፍያ እንደሚፈጽሙ በመረዳት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ ያሳስባ ፡፡

ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርአቱ የቆጣሪ ንባብ ጥራት ችግርን እና ግምታዊ አሞላልን ከማስቀረት ባለፈ ደንበኛው የውሃ ፍጆታውን በተጠቀመበት ወር ለመክፈል ያስችለዋል ፡፡

የንባብ ስርዓቱ ለዚሁ ተግባር ተብሎ አፕልኬሽን በተጫነባቸው የሞባይል ስልኮች አማኝነት የሚሰራ ሲሆን ቆጣሪ አንባቢው በደንበኛው ቤት ወይም ድርጅት በሁለት ሜትር ክልል ውስጥ ካልተገኘ በስተቀር ሲስተሙ አያነብለትም፤ ይህም በስፍራ ተገኝቶ ትክክለኛ መረጃ እንዲያስገባ ያስገድደዋል፡፡

ይቨው ቴክኖሎጂ በቀጣይም በቀሩት 4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር በሚገኙ የባለስልጣኑ ደንበኞች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል ፡፡