ባለስልጣኑ የመዲናዋን የመጠጥ ዉሃ እጥረት ለመቅረፍ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ወደ ስርጭት የሚገቡ የውሃ ልማት አማራጮች ላይ እቅድ በመያዝ ተግባራዊ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሰረት በተያዘው በጀት አመት በአጭር ጊዜ ወደ ስርጭት ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁ 49 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን በማልማት መቶ ሺህ (100,000) ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማረት እቅድ ይዞ ነዉ እየሰራ የሚገኘው ፡፡
ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ በጥቅሉ ከነባር የገጸ-ምድር ፣ የከርሰ-ምድር እና አዳዲስ የውሃ አማራጮችን ጨምሮ ሁለት መቶ ስምንት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማምረት ለማሰራጨት አቅዷል፡፡