የመስመር ቅየራ የተደረገው በባለስልጣኑ 8 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ሲሆን ባለፉት ስምንት ወራት 28 ኪ.ሜ መለስተኛ መስመር ለመቀየር ታስቦ የዕቅዱን 94.41% ማከናወን ተችሏል፡፡
ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩና ያረጁ የብረት መስመሮች በፕላስቲክ የውሃ መስመሮች መቀየራቸው ባለስልጣኑ አምርቶ የሚያሰራጨውን ንፁህ ውሃ ከብክነት እና ብክለት በማዳን በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 43 ኪሎ ሜትር መለስተኛ የውሃ መስመር በአዲስ ለመቀየር ዕቅድ ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች