በባለስልጣኑ ይዞታ በሆኑት በለገዳዲ እና ድሬ ግድቦች ዙሪያ የተተከሉት ችግኞች የአፕል፣ የሀበሻ ፅድ፣ የፈረንጅ ፅድ እና የግራቪሊያ ዝርያ ያላቸው ናቸው፡፡

ከነዚህም ውስጥ 23,150 ችግኞች ፅድ እና ግራቪሊያ እንዲሁም 6 ሺህ 70 የሚሆኑት የአፕል ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከባለስልጣኑ ችግኝ ማፍያ እና ከችግኝ አቅራቢ ተቋም በግዢ የተገኙ ናቸው፡፡

የተተከሉትን የአፕል ችግኞች ለማፅደቅ ባለስልጣኑ የውሃ ማጠራቀሚያ የማዘጋጀት፣ የውሃ መስመር መዘርጋት እና ማዳበሪያ የማቅረብ ስራ ያከናውናል፡፡

የአከባቢው አርሶ አደሮች ችግኞቹን በዕጣ በመከፋፈል ውሃ የማጠጣት፣ የመኮትኮት እና የመንከባከብ ስራውን በማከናወን ከሚያፈሩት ፍሬ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ለተቀሩት ችግኞችም ተንከባካቢ የሚመደብላቸው ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ እንደሚፀድቁ ይገመታል፡፡