ስምምነቱ የተፈረመው በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ቪተንስ ኢቪደስ ኢንተርናሽናል ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር ነው ፡፡
በስምምነቱ መሰረት በ9.3 ሚሊየን ዩሮ በላይ በሆነ ወጪ በድሬ እና ለገዳዲ ተፋሰሶች ለሚኖሩ ነዋሪዎች የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ አቅርቦትን የማሻሻል ስራ ይሰራል፡፡
በሰምምነቱ በዕቅድ ከተያዙ ተግባራት መካከል በተፋሰስ ልማት እና አጠቃቀም ላይ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል እና በፌዴራል ተቋማት መካከል የክልል ተሻጋሪ ውይይትን ማጎልበት፣ የለገዳዲ እና ድሬ የግድቦችን ውሃ የመያዝ አቅም ዘላቂነት ማሻሻል የግድብ የውሃ ጥራትን ማስጠበቅ እንዲሁም የደለል መጠንን በመቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በተጨማሪም በድሬ እና በገዳዲ ግድቦች ተፋሰስ ኣካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ገበያ ተኮር የኑሮ ማሻሻያ ዕድሎችን በመፍጠር እና የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሥራዎችን በማበረታታት የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት የማሳደግ ስራ ይገኙበታል፡፡
በፕሮጀክቱ የለጋዲዲ እና የድሬ ግድብ አካባቢ የሚኖሩ 10 ሺህ ነዋሪዎች እንደዚሁም በእነዚህ የውሃ ተፋሰስ ውስጥ እና በዙሪያዋ 5 ከተሞች ማለትም የአቃቂ ፣ ቡራዩ ፣ ገላን ፣ ሱሉልታ እና ሰንዳፋ የሚገኙ 90 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን እ.ኤ.አ ከጥር ከ2020 እስከ ታህሳስ 2024 (በአምስት አመት) ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃለው፡፡
ስራው ከሚሰራባው አካባቢዎች መካከል የድሬ ተፋሰስን በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ምክትል አምባሳደር፣ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ፣ በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በረክ ወረዳ ፣ በቪቴንስ ኢቪደስ ኢንተርናሽናል አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል፡፡