ዛሬም በባለስልጣኑ ዋናው መስሪያ ቤት “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ” በሚል መሪ ቃል ደም ለግሰዋል፡፡
በመረሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ወርቁ አንዱዓለም የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ዓላማ የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ሀገር አፍራሾችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ሰራተኛው የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ሊቀመንበሩ የባስልጣኑ ሰራተኞች ወቅታዊውን የሀገራችንን ሁኔታ በውል በመረዳት እንደ ዜጋ ሀገራዊ ግዴታቸውን በመወጣት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
ደም የለገሱት የባለስልጣኑ ሰራተኞችም በበኩላቸው “በድል እየገሰገሰ የሚገኘው መከላከያ ሰራዊታችን እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎኑ እንቆማለን” ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።
ባሳለፍነው ሳምንትም የደም ልገሳው መረሃ ግብር በባለስልጣኑ ቅርንጫፎች ተከናውኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡