ውይይቱም በውሃ ፣ ፍሳሽ እና ደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ስራዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የባስልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ኢ/ር ዘሪሁን አባተ ከህዝብ ክንፍ የተውጣጡ የፎረም አባላት በባለስልጣኑ የስራ እንቅስቃሴ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመንቀስ ብሎም የመፍትሄ አካል በመሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በውሃ እና ፍሳሽ ዘርፍ ህብረተሰቡን የሚያረካ አገልግሎት ለመስጠት በሚደረገው ጥረት አጋዥ ሆነው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል፡፡
የደንበኞች ፎረም አባላቱም ውሃ እና ፍሳሽ ባስልጣን ከእቅድ ጀምሮ አባላቱ ጋር በመምከር ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
ውሃ አላቂ ሀብት ፣ በውድ ዋጋ የሚመረት ስርጭቱም ፈታኝ መሆኑን ተረድተና ያሉት አባላቱ ሁሉም ደንበኞች ዘንድ ለማስረጽ እንሰራለን ብለዋል ፡፡
በገቢ አሰባሰብ ረገድ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍም ከተቋሙ ጎን እንደሚሆኑ ያረጋገጡት ተሳታፊዎቹ ፤ በፍሳሽ አወጋገድ በኩል አነስተኛ የፍሳሽ ማንሻ ተሸከርካሪዎች እና ጄት ማስተር እጥረት በመፍታት በኩል ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡
ለውሃ ፈረቃ መዛባት ምክኒያት የሆኑ የመስመር ስብራት እና የኤሌትሪክ መቋራረጥ ችግሮችን ለመፍታትም ከመንገዶች ባስልጣን እና ከኤሌትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል ፡፡
ባጠቃላይ በተነሱ ሀሳቦች ላይ በዘርፉ ሀላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የፎረም አባላቱ ያነሷቸውን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰራ ተገልጿል ::