የጥናት እና ዲዛይን ስራው በዋናነት በከተማዋ ምስራቃዊ ክፍል በተለይም በቦሌ እና በየካ ክፈለ ከተሞች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

ፕሮጀክቱም በቀን ሰማንያ ሺ (80,000) ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ አጣርቶ የሚያሰወግድ ሲሆን አሁን በከተማዋ ያለውን ፍሳሽ በመስመር የማስወገድ ዝቅተኛ ሽፋን የሚሳድገው ይሆናል፡፡

አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ዲዛይንና ጥናት ከዓለም ባንክ በተገኝ 6.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እና ስድስት መቶ ሰማንያ ሺ (680,000) ብር የሚከናወን ነው፡፡

የጥናት እና ዲዛይኑን ስራ የሚያከናውኑት ኒኮላስ ኦድዌር የተሰኝ የአይርላንድ እና ኤምኤስ ሀገር በቀል አማካሪ ድርጅትቶች ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱን ስራ ዛሬ በይፋ የማስጀመር መረሀ-ግብር ላይ ከአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ እና ሳንቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን ቴክኒካ ማናጀር አቶ ደበበ ሙለታ፣ የአይርላንዱ ኒኮላስ ኦድዌር አማካሪ ድርጅት ምክትል ስራ-አስኪያጅ ፓትሪክ ሪለይ እንዲሁም ሀገር በቀሉ ኤም ኤስ አማሪ ድርጅት አስተባሪ አቶ መስፍን ሽንቁጥ ተገኝተው ፕሮጀክቱ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡

የጥናት እና ዲዛይን ስራው ተጠናቆ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራ ሲደረግ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡