የፕሮጀክቱ ሥም፡- የኮተቤ ፍሳሽ ማድረቂያ መደብ ማሻሻያ ፕሮጀክት

አስፈፃሚ አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፕሮጀክት ጽ/ቤት

ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ በአያት አካባቢ

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡በአያት አካባቢ የፍሳሽ መስመር ያልተደረሰባቸውን ክፍለ ከተሞችና አካባቢዎች እንዲሁም የተገነቡትንና አዲስ የሚገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች የፍሳሽ አገልግሎት በማዳረስ ከነዚህ አካባቢዎች የሚወጣው ፍሳሽ በጊዜያዊነት በኮተቤ ፍሳሽ ማድረቂያ ጣቢያ ለማጣራት እንዲቻል የኮተቤን ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ማሻሻያ ግንባታ ማከናወን ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ፡-

ከአያት አካባቢ ከሚገኙ የኮንደሚኒየም ቤቶች የሚወጣውን ፍሳሽ በጊዜያዊነት በኮተቤ ፍሳሽ ማድረቂያ ጣቢያ ለማጣራት እንዲቻል የማሻሻያ ግንባታ ሥራ ይጠናቀቃል፡፡

በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡

 • የነባር ማድረቂያ መደብ ማሻሻያ ስራ እና የአዳዲስ ማድረቂያ መደቦች ጥናት ማከናወን፣
 • የግንባታ ስራ ማከናወን፣

የሚጠበቅ ውጤት፡-

 • በአጠቃላይ ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሆኖ ሲጠናቀቅ በአያት አካባቢ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የኮንዶሚኒየም ቤቶች፣ ድርጅቶች እና ፋብሪካዎች የየሚወጣ ፍሳሽ በዘለቄታዊነት በኮተቤ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ተጣርቶ እንዲወገድ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-

 • በ 2006 ዓ.ም. ይጠናቀቃል፡፡

ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

 • በ 2007 ዓ.ም. ይጠናቀቃል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋጋ ግምት፡-

 • 25,623,000 እንደሚፈጅ ይገመታል፡፡

 

መግቢያ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋን የፍሳሽ አገልግሎት ለማሻሻል የነባር ማጣሪያዎችን የማሻሻል እና አዲስ ማጣሪያ ጣቢያዎችን የመገንባት ስራ በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በ2006/07 ዓ.ም ከአያት አካባቢ የሚወጣውን የፍሳሽ ቆሻሻ በዘለቄታዊነት በኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ አጣርቶ ለማስወገድ ያስችል ዘንድ የማጣሪያ ጣቢያውን የማጣራት አቅም ማሳደግ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ማሻሻያ ፕሮጀክት ተቀርጿል፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት፡-

በአያት አካባቢ የመኖሪያ፣ የድርጅቶች እና የኮንዶሚኒየም ግንባታዎች በስፋት እየተከናወኑ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አካባቢው በፈጣን እድገት በመልማት ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና እነዚህን እና ሌሎች አካባቢዎችን በማገልገል ላይ ያለው የኮተቤ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ከአካባቢዎቹ የሚወጣውን ተጨማሪ የፍሳሽ ቆሻሻ በዘለቄታዊነት አጣርቶ ለማስወገድ የሚያስችል አቅም  የለውም፡፡ በመሆኑም የማጣሪያ ጣቢያውን የማሻሻል ስራ ተጣርቶ የሚወገደውን የፍሳሽ ቆሻሻ ከማሳደግ በተጨማሪ በአካባቢው የተጀመረውን የልማት ስራ እንዳይደናቀፍ ከማድረግ አኳያ  ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ፡-

 • በአያት አካባቢ የፍሳሽ መስመር ያልተደረሰባቸውን ክፍለ ከተሞችና አካባቢዎች እንዲሁም የተገነቡትንና አዲስ የሚገነቡትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች የፍሳሽ አገልግሎት በማዳረስ ከነዚህ አካባቢዎች የሚወጣው ፍሳሽ በጊዜያዊነት በኮተቤ ፍሳሽ ማድረቂያ ጣቢያ ለማጣራት እንዲቻል የኮተቤን ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ማሻሻያ ግንባታ ማከናወን ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ግብ፡-

 • ከአያት አካባቢ ከሚገኙ የኮንደሚኒየም ቤቶች የሚወጣውን ፍሳሽ በጊዜያዊነት በኮተቤ ፍሳሽ ማድረቂያ ጣቢያ ለማጣራት እንዲቻል የማሻሻያ ግንባታ ሥራ ይጠናቀቃል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች፡-

 • ጤናው የተጠበቀና አምራች የሆነ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
 • የአካባቢው ልማት በይበልጥ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡

በ2008 በጀት አመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 • የመያዥያ ክፍያ መፈጸም

የክትትልና ግምገማ ሥርዓት፡-

የክትትል መመዘኛ ነጥቦችን በጨረታና በስምምነት ሰነዶች ላይ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡ የግንባታ ሥራም በሚጀመርበት ወቅት አማካሪው በሚያቀርበው የሥራ ክትትል ስልት መሠረት እና ባለቤቱ በሚመድባቸው መሃንዲሶች የሥራ ሂደት ክትትል ያደርጋል፡፡

ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች

ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችና ምቹ ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃል፡፡

የ2008 በጀት ፍላጎት

ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
50 የኮተቤ ፍሳሽ ማድረቂያ ጣቢያ ማሻሻያ ፕሮጀክት   582,667 0 582,667 0 0
50.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የማድረቂያ መደቦች ግንባታ ሥራ በማከናወን 23,306,696 582,667 582,667 አጠቃላይ ሥራው በቀሪ ጊዜ ውስጥ የሚያልቅ በመሆነ የሚያዝያ ክፍያ 2.5 በመቶ የሚሆነው ብቻ በ2008 ተይዟል፡፡