በምርቃት ሥነ-ሥርዐት ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማው መስተዳድር በጅምር ያሉትን የውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት አጠናቆ በመጨረስ የነዋሪውን ፍላጎት ማሟላት እንደሚገባ ገልፀው ይህም ሊሳካ የሚችለው በጋራ የመልማት መርህ ላይ ስንቆም መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኮዬ ፈቼ ቂሊንጦ ቱሉ ዲምቱ የውሃ ፕሮጀክት በ 2006 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው 1.2 ቢሊዮን ብር ፈጅቷል፡፡ፕሮጀክቱም በቀን 44 ሺህ ሜትር ኪዩብ ንፅህ የመጠጥ ውሃ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ፣በኮዬ-ፈቼ እና ቅሊንጦ አካባቢ ለሚገኙ ለ440 ሺህ በላይ ለሚደርሱ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ፕሮጀክቱ 9 ጥልቅ ጉድጓዶችን፣ 2 የማጠራቀሚያ ጋኖች ግንባታን፣ የ29.1 ኪ.ሜ ማሰባሰቢያ መስመር፣ የፖምፕ እና ተያያዥ የሲቪል ስራዎችን እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃ አቅርቦትና ተከላ ስራዎችን ያካትታል፡፡