የኘሮጀክቱ ሥም፡ የዋናው መ/ቤት ላቦራቶሪና የቃሊቲ ፍሳሽ ላቦራቶሪ እቃዎችና መሳሪያዎች ማሟላት ፕሮጀክት
አስፈፃሚው አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት
ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- በዋናው መ/ቤትና በቃሊቲ፡፡
ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- የውኃና ፍሳሽ ጥራትን መጠበቅ እና የግንባታ መሳሪያዎችን በመግዛት ለመሳሪያ ኪራይ የሚወጣውን ወጪ መቀነስ ነው፡፡
የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- ለግንባታ የሚያገለግሉ ማሽኖች በመግዛት ለማሽን ኪራይ የሚወጣውን ወጪ እንዲቀንስ ይደረጋል፡፡
በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- የላቦራቶሪ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ግዥ፣
- የማውንት ክሬን፣ ኤክስካቫተር ጃክሀመር፣ሻወር ትራክ (16ሜ ኩብ) እና የ5 ዳም ትራክ (5ሜ. ኩብ) ግዥ መፈጸም
ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-
- በ2001 ዓ.ም.
ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-
- በ2008 ዓ.ም.
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 46,858,406 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- የቀሪ 9 የመስክ ተሸከርካሪዎች ግዥ ማጠናቀቅ፣
- 50 የውኃ ቦቴ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ማጠናቀቅ፣
- የቀሪ 2 ማሽነሪዎች ግዥ ማጠናቀቅ፣
- በ2 ወር ጊዜ ውስጥ እስከ ነሐሴ ወር ኤልሲ በማስከፍት የ8 ሰራተኞች ሰርቪስ መኪና አቅርቦት ሥራ ማጠናቀቅ፣
ለ2008 በጀት ዓመት የሚያስፈልግ በጀት ማጠቃለያ
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
39 | የዋናው መ/ቤት ላቦራቶሪና የቃሊቲ ፍሳሽ ላቦራቶሪ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ማሟላት ፕሮጀክት | 49,884,098 | 49,884,098 | 0 | 0 | 0 | ||
39.1 | የቀሪ 9 የመስክ ተሸከርካሪዎች ግዥ ማጠናቀቅ፣ | 6,750,000 | 6,750,000 | 6,750,000 | ለቀሪ 9 መኪኖች ግዥ ለማጠናቀቅ የተያዘ በጀት ሲሆን ለ1ዱ መኪና 750ሺህ ብር ተይዟል፡፡ | |||
39.2 | የቀሪ 2 ማሽነሪዎች ግዥ ማጠናቀቅ፣ | 3,307,373 | 3,307,373 | 3,307,373 | ከዚህ በፊት ለቀሪ 2ቱ ማሽነሪዎች በተገባው ውለታ መሠረት የሚከፈል ክፍያ ነው | |||
39.3 | 50 የውኃ ቦቴ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ማጠናቀቅ፣ | 11,181,037 | 7,826,725 | 7,826,725 | ቀሪ 70 በመቶ ክፍያው በ2008 በጀት ዓመት በተገባው ውለታ መሠረት ለመክፍል የተያዘ በጀት ነው፡፡ | |||
39.4 | የ8 ሰራተኞች ሰርቪስ መኪና አቅርቦት ሥራ ማጠናቀቅ | 4,000,000 | 32,000,000 | 32,000,000 | ከመኪና አቅርቦቱ ጋር በተያያዘ በ2008 በጀት ዓመት ለሚከፈል ክፍያ የተጠቀሰው ብር ተይዟል፡፡ ለበጀቱ መነሻ ከመከላከያ ጋር በቅርቡ የገቡት 2 መኪኖች ዋጋ ታሳቢ ተደርጓል፡፡ |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች