የኘሮጀክቱ ሥም፡            የውኃ ቆጣሪ እና የውኃ ብክነት መመርመሪያ መሣሪያ ግዥ መፈጸም ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል፡-         በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት

ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡-ለዋ/መ/ቤት እና ቅ/ጽ/ቤቶች

ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- ቆጣሪዎችን በተገቢው ደረጃ በመፈተሽ እና በተለያዩ ምክንያት በየቦታው የሚፈሰውን ውኃ በመቆጣጠር ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ፈሶበት የተመረተውን ውኃ ከብክነት ማዳን፡፡

የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- አዲስ የሚገዙ ቆጣሪዎችን እና አግልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ቆጣሪዎችን በተገቢው ደረጃ በመፈተሽ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈሰውን ውኃ በመቆጣጠር ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ፈሶ የተገኘውን ውኃ ከብክነት ማዳን፡፡

በኘሮጀክቱ የሚከናወን ዋና ተግባር፡-

  • ለቆጣሪ ምርመራ (Automatic Test Bench) እና ለውኃ ብክነት ምርመራ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች (የድምጽ መመዝገቢያ/Noise Looging Equipment) ግዥ መፈጸም፣
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የቴስት ቤንች እቃዎች ማስቀመጫ ቤት ግንባታ ማናወን
  • የማንሆል ግንባታ
  • የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ2 ተጨማሪ ቴስት ቤንች እቃዎች ማስቀመጫ ቤት ግንባታ ማናወን

ኘሮጀክቱ የሚጀመርበት ጊዜ፡-

  • በ 2005 ዓ.ም.

ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-

  • በ 2008 ዓ.ም.

የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት፡- 76,500,000 ይፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡

መግቢያ

ባለሥልጣን መ/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት እያመረተ ካለው ጠቅላላ ውኃ ውስት 37% የሚሆነው ማለትም የገፈርሳ ግድብ እያመረተ ያለውን የውኃ መጠን በእጥፍ የሚበልጠው የውኃ መጠን በተለያዩ ምክንያቶች እየባከነ በመሆኑ ይህንን ብክነት መቀነስ አንድ የውኃ ምንጭ እንደመገንባት በመሆኑ በዚህ በጀት ዓመት የብክነን የሚጠቁም መሣሪያ እና የቆጣሪዎችን ደህንነት የሚፈትሽ መሣሪያዎችን ግዥ ለመፈጸም ፕሮጀክቱ ተቀርጿል፡፡

የግዥው አስፈላጊነት

ብነትን መቆጣጠር ከፈተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ድሀ ሀገሮች ደግሞ ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ሲሆን፣ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ሆኖበት የተጣራ ውሃና ካለምንም ጥቅም በመሬት ውስጥ መፍሰስ የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ያስቀራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገቢ ከማይሰበሰብባቸው የውሃ አገልግሎቶች ገቢ በመሰብሰብ የድርጅቱን ገቢ ማሣደግ ያስችላል፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

ይሄ ኘሮጀክት የከተማውን የውኃ አቅርቦት እና ሥርጭት ከማሳደጉም በተጨማሪ ገንዘብ የማይሰበሰብበትን የውኃ መጠን በመቀነስ የመ/ቤቱን ገቢ እንዲያድግ ያደርጋል፡

2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የማንሆል ክዳን ማስቀመጥ ሥራ ማከናወን
ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
45 የውኃ ቆጣሪ እና የውኃ ብክነት መመርመሪያ መሣሪያ ግዥ መፈጸም ፕሮጀክት   1,372,194 0 1,372,194 0 0
45.1 የማንሆል ክዳን ማስቀመጥ ሥራ ማከናወን 5,276,004 1,372,194 1,372,194 አጠቃላይ ቀሪ የማንሆል ግንባታ ሥራው ማለትም ከ57ቱ 33ቱ የግንባታ ሥራው ሙሉ በሙሉ ያለቀ ሲሆን ቀሪው ሥራ ግን የውኃ ሥርጫቱን ላለመረበሽ ሲባል ወደ 2008 በጀት ዓመት ተዘዋውሮ የሚሰራ በመሆኑ በዚህ መነሻነት ቀሪ ክፍያው ወደ ቀጣ በጀት ዓመት ሊዘዋወር ችሏል፡፤