ጉብኝት ያካሄዱት በዓለም ባንክ የውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ስራአኪያጅ ማሪያ አንጀሊካ እና በአለም ባንክ የሁለተኛው የከተሞች የውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አስተባባሪዎች አንቶኒ ሬዴግሩዝ እና ሀባብ ታይፉር ናቸው፡፡

የተጎበኙት መሰረተ ልማችም ቃለቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ፣ በለገዳዲ እና ድሬ ግድቦች ናቸው ፡፡

የዓለም ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ የውሃ እና ፍሳሽ መሰረተ ልማቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሀላዎቹ በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡

ሀላፊዎቹ ከውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማቶች በተጨማሪ የባለስልጣኑን የማሰልጠኛ ማዕከል የጎበኙ ሲሆን ባለስልጣኑን የሰራኛውን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ እየሰጠ ያለውን የመሪነት ስልጠና (FLL) እንደሚደግፍ አረጋግጧል ፡፡