በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በጉርድ ሾላ ፣መካኒሳ ፣ንፋስ ስልክ እና አቃቂ ቅ/ጽ/ቤቶች ስር በሚገኙ ከሶስት መቶ ሺ (300,000)በላይ ደንበኞች ከነገ ጀምሮ በዘመናዊ ቆጣሪ ንባብ ስርዓት የተነበበውን ክፍያ መክፈል ይጀምራሉ፡፡

የቆጣሪ ንባብ ስርዓቱ በዋናነት ከግምታዊ አሞላል ከመላቀቅ ባሻገር ከዚህ ቀደም ደንበኞች ሁለት ወር ወደ ኋላ ተመልሰው የሚከፍሉትን አሰራር አስቀርቶ በየወሩ የፍጆታ ክፍያቸውን እንዲከፍሉ የሚያስችል ነው ፡፡

በተለይ በዚህ ወር የቆጣሪ ንባብ ስርዓቱ ተጠቃሚ የሆናችሁ ደንበኞች የሁለት ወር የውሃ ፍጆታ ክፍያ እንደምትከፍሉ አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ባለስልጣኑ ያሳስባል፡፡

ቀደም ባሉ ወራት የአራዳ፣ ጉለሌ፣አዲስ ከተማ እና መገናኛ ቅ/ ጽ/ቤቶች ተጠቃሚ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡

የውሃ ፍጆታ ክፍያችሁን ለማወቅም በዌብሳይታችን www.aawsa.gov.et በመግባት የቢል መረጃ የሚለውን ክሊክ በማድረግ እና የደንበኛ መለያ ቁጥር በማስገባት እንዲሁም በCBE birr አማካኝነት የክፍያ መጠን ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የክፍያ ጊዜውም ሁሌ በወር መጨረሻ ከ26 እስከ 18 መሆኑን እንገልጻለን

የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን