የፍሳሽአገልግሎት ማሻሻያ ልማት ሥራዎች
የባለሥልጣን መ/ቤቱ ለከተማዋ ህብረተሰብ የፋሳሽ ቆሻሻ ማንሳት አገልግሎት በ2 መንገድ የሚሰጥ ሲሆን ይህም በፍሳሽ ተሸከርካሪ እና በዘመናዊ ፍሳሽ መስመር ነው፡፡ በመሆኑም በ2010 በጀት ዓመት ይህን አገልግሎት ከማሻሻል እና ከማስፋፋት አንጻር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ዋና ዋናዎቹም
- የጨፌ ክፍል 1 ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት
- የጨፌ ክፍል 2 ፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ፕሮጀክት
- የደቡብ አቃቂ ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት
- የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት
- የምስራቅ ተፋሰስ የፍሳሽ ማጣሪያ እና መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት
- በኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ያልተማከለ ፓኬጅ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ግንባታ ማከናወን
ከፍሳሽ ልማት ስራዎች አንጻር በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረዥም ጊዜ እስከ 340.5ሺህ ሜኩብ ፍሳሽ በቀን የማጣራት አቅም እንደሚፈጠር ይጠበቃል፡፡
ተ.ቁ | የፕሮጀክቶችዝርዝር | የሚጠበቅ የማጣራት አቅም በሜኩብ | ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ዝግጁ የሚሆንበት ጊዜ |
1 | የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት | 100,000 | 2010 |
2 | በኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ግንባታ ማከናወን | 27,000 | 2010 |
3 | ኮዬ ፍጪ ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት | 33,000 | 2010/11 |
4 | በ4 ኮንዶሚኒየም ሳይቶች (ቦሌ አራብሳ 3፣ 4፣ 5 እና 6) ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት | 15,500 | 2011/12 |
5 | የጨፌ ክፍል 1 ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት | 12,500 | 2010 |
6 | የጨፌ ክፍል 2 ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት | 12,500 | 2011/12 |
7 | የደቡብ አቃቂ ፍሳሽ ማጣሪያና የፍሳሽ መስመር ጥናትና ግንባታ ፕሮጀክት | 60,000 | 2014 |
8 | የምስራቅ ተፋሰስ የፍሳሽ ማጣሪያ እና መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት | 80,000 | 2014 |
አጠቃላይ በአጭር፣ መካከለኛ እና ረዥም ጊዜ ከፍሳሽ ልማት ስራዎች የሚጠበቅ ውጤት | 340,500 |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች