የፕሮጀክቱ ሥም፡ የፍሳሽ ተሸከርካሪ ፍሊት ማኔጅመንት ፕሮጀክት

አስፈፃሚው አካል ፡ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ ፡ በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎቻችን/በቃሊቲ፣በኮተቤ፣በገላን፣በሚኪሊ ላንድ፣በላፍቶ ኢንጀክሽን ፖይንት/ እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን

የስራው ጠቅላላ አላማ ፡ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የፍሳሽ የማሰባሰብ እንዲሁም የማጣራት ሂደታችን የሚገልፅ የመረጃ አያያዛችን በጣም ኋላቀር ስለሆነ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖረን ለማስቻል ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ግብ ፡ በ2006-08 ዓ.ም በጀት ዓመት በመ/ቤታችን የሚታየውን የፍሳሽ የማሰባሰብ እንዲሁም የማጣራት ሂደታችን የሚገልፅ የመረጃ አያያዛችን በጣም ኋላቀር ስለሆነ ይህንን ችግር ሊቀርፍ የሚችል ጥናት በማጥናትና ወደ ተግባር በመግባት በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የፍሳሽ የማሰባሰብ እንዲሁም የማጣራት ሂደታችን ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖረን ለማስቻል ነው፡፡

የሚከናወኑ ተግባራት፡

  • አስፈላጊውን ጥናት ማጥናት
  • በተጠናው ጥናት መሰረት ወደ ተግባር መግባት

ፕሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡ 2006 ዓ.ም

ፕሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡ 2008 ዓ.ም

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት ግምት፡ 10,000,000.00 ብር

መግቢያ

የፍሳሽ ቆሻሻ ማሰባሰብ፣ማጣራት እና በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ማስወገድ ደግሞ በፍሳሽ ቆሻሻ አስተዳደር ውስጥ ከሚታዩት ባህሪያቶች ውስጥ የመታወቁት ሲሆኑ በተለይ የመረጃ አያዝ ስርዓቱ ደግሞ የተጠናከረ ከሆነ የፍሳሽ ቆሻሻ አስተዳደር ሂደቱ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በመ/ቤታችን ተጨባጭ ሁኔታ የመረጃ አያያዝ ስርዓታችን ኋላቀር ከመሆኑ ተነሳ የሚፈለገው መረጃ በተፈለገ ጊዜና ሰዓት የማይገኝበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የፍሳሽ የማሰባሰብ እንዲሁም የማጣራት ሂደታችንን የሚገልፅ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖረን ለማስቻል የዚህ ጥናት መተናት እና ተግባራዊ ማድረግ ከምንም በላይ ጠቀሜታው እጀግ ብዙ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

ሥራው፡-

  • በማጣሪያ ጣቢያዎቻችን እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን የሚታየውን የመረጃ አያያዝ ችግር ይቀርፍልናል፣
  • በአንድ ቀን ውስጥ ምን ያህል ፍሳሽ እንዳሰባሰብን እና እዳጣራን እና መልሰን እንደተጠቀምን እንዲሁም እንዳስወገድን በቂና አሳማኝ መረጃ እናገኛለን፡፡
  • የመረጃ አያያዛችን የተቀላጠፈ ከመሆኑ የተነሳ ማንኛውም አካል መረጃ ቢፈልግ/ ብንፈልግ በቀላሉ ማግኘትና መተንት እንችላለን፡፡

የፕሮጀክቱ አላማ

  • በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎቻችን እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን ያለውን የማጣራት ሂደት እና የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን ዘመናዊ ሊያደርግ የሚያስችል ጥናት ማካሄድ እና ተግባራዊ ማድረግ፤

የፕሮጀክቱ ግብ

  • ለስራው የሚያስፈልጉ ማናቸውም ግብዓቶችን በመጠቀም በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎቻችን እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን ያለውን የማጣራት ሂደት እና የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን ዘመናዊ ሊያደርግ የሚያስችል ጥናት ማካሄድ እና ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች

  • በማጣሪያ ጣቢያዎቻችን እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን የሚታየውን የመረጃ አያያዝ ችግር ይቀርፍልናል፣
  • በአንድ ቀን ውስጥ ምን ያህል ፍሳሽ እንዳሰባሰብን እና እዳጣራን እና መልሰን እንደተጠቀምን እንዲሁም እንዳስወገድን በቂና አሳማኝ መረጃ እናገኛለን፡፡
  • የመረጃ አያያዛችን የተቀላጠፈ ከመሆኑ የተነሳ ማንኛውም አካል መረጃ ቢፈልግ/ ብንፈልግ በቀላሉ ማግኘትና መተንት እንችላለን፡፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  • በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎቻችን እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን ያለውን የማጣራት ሂደት እና የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን ዘመናዊ ሊያደርግ የሚያስችል ጥናት በጥቅል ማካሄድ እና መተግበር፤

የአፈፃፀም ስልቶች

  • የጥናትና ትግበራ ስራውን በዘርፉ ልምድ ላላቸው አማካሪዎች እና ተጫራቾች ለመስጠት በመመዘኛው መስፈርት መሰረት ተጫረቾች ይገመገማሉ፣ለአሸናፊው ስራው ይሰጣል፤

ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የግንባታ ግብዓቶች

  • ዘመናዊ የጥናትና የትግበራ ግብዓቶችን በጥቅል መጠቀም፡፡

የአካባቢና ማህበራዊ ትንታኔ

  • ፕሮጀክቱ የታሰበውን የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን በእጅጉ የሚቀርፈው ሲሆን ወደ ቅብብሎሽ ጣቢያዎች ለመግባትና ስራውን ለመስራት በሚደረገው እንቅስቃሴ የቦታ ይገባኛል እና የካሳ ክፍያዎችን በተመለከተ መለስተኛ የማህበራዊ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡

የክትትልና የግምገማ ስርዓት

  • ፕሮጀክቱ በሳምንታዊና በወርሃዊ በሚቀርቡ ሪፖርቶች ይገመገማል፤
  • ፕ/ጽ/ቤቱ ለፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ በመመደብ ሥራውን በቅርበት ይከታተላል፤
  • የፕሮጀክቱን ውጤትና የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች

  • ፕሮጀክቱ የሚያጋጥሙት ስጋቶች
  • የበጀት፣ የባለሙያ እና የትግበራ ዕቃዎች እጥረት ናቸው፡፡
  • ምቹ ሁኔታዎች
  • መንግስት የከተማው የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የፍሳሽ መስመር አወጋገድ ዘዴ እንዲቀየር እያደረገ ባለው ሂደት ውስጥ በዘመናዊ የፍሳሽ መስመር አወጋገድ ዘዴ የሚሰበሰበው የፍሳሽ መጠን ከፍተኛ ስለሚሆን በፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎቻችን እና በቅብብሎሽ ጣቢያዎቻችን ያለውን የማጣራት ሂደት እና የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን ዘመናዊ እንዲሆን ትኩረት በመስጠቱ፤

በጀት

  • ለፕሮጀክቱ በጠቅላላው 10,000,000.00 ብር በጥቅል ተይዞለታል፡፡
ተ.ቁ. የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት የተያዘ በጀት ምርመራ
ከመንግስት ከመ/ቤቱ ከብድር ዕርዳታ
22 የፍሳሽ ተሸከርካሪ ፍሊት ማኔጅመንት ፕሮጀክት   10,000,000 10,000,000 0 0 0
22.1 የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የፍሳሽ ተሸከርካሪ ፍሊት ማኔጅመንት ሥራ ማከናወን 10,000,000 10,000,000 10,000,000 በ2007 በጀት ዓመት ተይዞ የነበረው የ2 ሚሊዮን ብር  በጀት  ብቁ  አጥኚ ድርጅት በማወዳደር ለመቅጠር  እንዲሁም ለስራው የሚያስፈልጉ  ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም የሚያስችል ባለመሆኑ በ2008  በጀት  10 ሚሊዮን ብር ተደርጎ ተይዟል፡፡ አጠቃላይ ሥራው 6 ወር የሚፈጅ ነው፡፡