የኘሮጀክቱ ሥም፡ የ GW1፣ GW2፣ new CT፣ old CT ለገዳዲ እና ገፈርሳ ግቢ የማስዋብ እና አጥር ግንባታ ፕሮጀክት
አስፈፃሚው አካል፡- በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኘሮጀክት ጽ/ቤት
ኘሮጀክቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- GW1፣ GW2፣ new CT፣ old CT ለገዳዲ እና ገፈርሳ ግቢዎች ውስጥ
ኘሮጀክቱ ጠቅላላ ዓላማ፡- ባለስልጣን መ/ቤቱ በከፍተኛ ወጭ የሚያስገነባቸውን የውሃ ግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና ማጠራቀሚያ ጋኖች የግቢ ይዞታዎች ጽዳት እና ውበት እንዲኖራቸው ማድረግ
የኘሮጀክት አጠቃላይ ግብ፡- ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የውሃ ግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና ማጠራቀሚያ ጋኖች የሚገኙባቸው ግቢዎች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ አስፋልት እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም አጥር እንዲገነባቻለው በማድረግ ግቢዎቹ ጽዳት እና ውበታቸውን እንዲጠብቁ ይደረጋል፡፡
በኘሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
- በራስ ሀይል የጥናት ስራ ማከናወን
- የተቋራጭ ቅጥር በመፈጸም የ GW1፣ GW2፣ new CT፣ old CT ለገዳዲ እና ገፈርሳ አጥር ግንባታ፣ ኮንክሪት አስፋልት ስራ እና ግቢውን የማስዋብ ስራ ማከናወን
ከኘሮጀክቱ የሚጠበቅ ውጤት
- ይህ ኘሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን ከፍተኛ ወጭ ወጥቶባቸው የተከናወኑ ግንባታዎች የሚገኙባቸው ግቢዎች ላይ ግቢ ማስተካከል ግንባታ ስራ ተሰርቶ ደረጃቸውን እንዲጠብቁ ይደረጋል፡፡
ኘሮጀክቱ የተጀመረበት ጊዜ፡-
- በ 2006 ዓ.ም.
ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ጊዜ፡-
- በ 2007 ዓ.ም.
የኘሮጀክቱ ጠቅላላ በጀት
- 40,000,000 የፈጃል ተብሎ ይገመታል፡፡
መግቢያ
ባለስልጣን መ/ቤቱ የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከራሱ ገቢ እና ከከተማ አስተዳደሩ በጀት በማስመደብ ዘርፈብዙ የሆነ የከርሰምድር እና የገጸ ምድር ውሃ ልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መነሻነትም የተለያ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ በዚህም ተጨባጭ ውቴት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
እነዚህ በከፍተኛ ወጭ የተፈጸሙ ግንባታዎች የሚገኙባቸው ግቢዎች ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና በስራ ላይም እንቅፋት እየፈተሩ ያሉበት ሁኔታ እየተስተዋለ መሆኑን መነሻ በማድረግ በቀጣይ ግቢውን ለአገልግሎት ምቹ ለማድረግ እንዲያስችል ይህን ፕሮጀክት መቅረጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የኘሮጀክቱ ዓላማ
ባለስልጣን መ/ቤቱ በከፍተኛ ወጭ የሚያስገነባቸውን የውሃ ግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና ማጠራቀሚያ ጋኖች የግቢ ይዞታዎች ጽዳት እና ውበት እንዲኖራቸው ማድረግ
የኘሮጀክቱ ግብ
ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የውሃ ግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና ማጠራቀሚያ ጋኖች የሚገኙባቸው ግቢዎች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ አስፋልት እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም አጥር እንዲገነባቻለው በማድረግ ግቢዎቹ ጽዳት እና ውበታቸውን እንዲጠብቁ ይደረጋል፡፡
የሚጠበቅ ውጤትና ተጠቃሚዎች
ይህ ኘሮጀክት ሲጠናቀቅ በአሁን ሰአት ቦኤፖሬሽን ስራ ላይ የተፈጠረውን ችግር ከመቅረፉም ባሻገር ለግንባታዎቹ ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
በኘሮጀክቱ ሂደት የሚጠበቁ ውጤቶችና ተጠቃሚዎች መካከል
- በኘሮጀክቱ አካባቢ ለሚገኙ የከተማ ነዋሪዎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል ይከፍታል፣
- የጥቃን እና አነስተኛ ተቋማትን ተሳትፎ (በጽዳት፣ አትክልት ስራ እና ማስዋብ) ያጎለብታል፡፡
ከኘሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላ የሚገኙ ውጤቶችና ጥቅሞች
- በአሁን ሰአት በተለይ በግድቦች ኦፕሬሽን ስራ ላይ አሉታ ተጽእኖ እያሳደረ የሚገኘውን ሁኔታ በመቅረፍ ምቹ የሆነ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል
- በከፍተኛ መዋለነዋይ የተገነቡ የውሃ ተቋማትን ገጽታ ከመገንባታ አኳያ የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
- የአ/አ ከተማን አለምአቀፋዊ እሴት ይበልጥ ያስጠብቀል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት
- የመያዥያ ክፍያ መፈጸም
የአፈጻጸም ስልቶች
- በፕሮጀክቱ ትግበራ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማትን ተሳትፎ በማሳደግ ፕሮጀክቱ ኢከኖሚያዊ ፋይዳ እንዲረውም ጭምር ማድረግ
- ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍተር ስራዎች በታለመላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማድረግ
- የፕሮጀክቱ ትግበራ በጠንካራ የክትትል እና ድጋፍ ስርአት እንዲደገፍ ማድረግ
ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግበአቶች
- ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሚያስፈልጉ የተለያየ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች፣
- የግንባታ ግብአቶች እና ማሽነሪዎች
- ፕሮጀክቱን ለመተግበር የሚያስፈልግ በጀት
የአካባቢና የማህበራዊ ትንታኔ
በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ የውሃ ልማት ተቋማትን ለአገልግሎት ምቹ ለማድረግ ተብሎ የተቀረጸው ይህ ኘሮጀክት ከታሰበበት የዋና አገልግሎት በተጨማሪ የሚሰራበትን አካባቢ ውበት እንዲኖረው ለማድረግም ጭምር የሚያገለግል በመሆኑ መልካም የሆነ የአካባቢና ማህበራዊ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
ስራው የሚከናወነው በባለስልጣኑ ይዞታ ስር በሚገኙ ቦታዎች ላይ በመሆኑ ከህብረተሰቡ ጋር የሚገናዥ የካሳ እና መሰል ጉዳች የማይኖሩት ይሆናል፡፡
የክትትልና ግምገማ ስርዓት
የኘሮጀክቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የታቀደለትን ጊዜ የጠበቀና ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን የሪፖርት፣ የሳይት ጉብኝት እና መሰል የክትትልና የግምገማ ሥርዓት የሚዘረጋ ይሆናል፡፡
አጠቃላይ እና ዝርዝር በጀት
ተ.ቁ. | የፕሮጀክቱ ሥምና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት | የውል ስምምነቱ መጠን/ኢንጂነሪግ ዋጋ ግምት | ለ2008 በጀት ዓመት የተያዘ በጀት | የተያዘ በጀት | ምርመራ | |||
ከመንግስት | ከመ/ቤቱ | ከብድር | ዕርዳታ | |||||
44 | የGW2፣ new CT እና old CT አጥር ግንባታ እና ግቢውን የማስዋብ ፕሮጀክት | 1,500,000 | 0 | 1,500,000 | 0 | 0 | ||
44.1 | የመያዥያ ክፍያ መፈጸም | 4,266,937 | 1,500,000 | 1,500,000 | አጠቃላይ ሥራው 95 በመቶ በ2007 በጀት ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን ቀሪ ክፍያ እና የመያዥያ ክፍያ ወደ 2008 በጀት ዓመት ተዘዋውሮ ተይዟል፡፡ |
የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች